የኮንስትራክሽን ሥራዎች ቁጥጥር ባለሥልጣን ላፕ ቶፕ ኮምፒተር፣ ዴስክ ቶፕ ኮምፒውተር፣ ዲጂታል ካሜራና ተጓዳኝ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Tender
< Back

የኮንስትራክሽን ሥራዎች ቁጥጥር ባለሥልጣን ላፕ ቶፕ ኮምፒተር፣ ዴስክ ቶፕ ኮምፒውተር፣ ዲጂታል ካሜራና ተጓዳኝ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

የኮምፒውተሮችና ተጓዳኝ ዕቃዎች ግዥ 

ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ 

የግዥ መለያ ቁጥር ኮ/ስ/ተ/ባግ/ጨ/003/2012 

የኮንስትራክሽን ሥራዎች ቁጥጥር ባለሥልጣን ከዚህ በታች በሠንጠረዡ የተገለፁትን ላፕቶፕ ኮምፒውተሮች፣ ካሜራዎችንና…ወዘተ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ስለሚፈልግ፡፡

/

ምድብ

የዕቃው አይነት

ብዛት

የጨረታ ማስከበሪያ/ ብር/

1

ሎት 1

ላፕ ቶፕ ኮምፒተር

10

5000.00

 

 

ዴስክ ቶፕ ኮምፒውተር

1

2

ሎት 2

ዲጂታል ካሜራና ተጓዳኝ ዕቃዎች

2

ተጫራቶች፦ 

  1. በየዘርፉ በቀጥታ የተሰማሩ ሆነው የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር(Tin Number) እና የግብር ክሊራንስ ማረጋገጫ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል። 
  2. በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በአቅራቢነት ዝርዝር የተመዘገቡበትን ማስረጃ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢነት ሠርተፍኬት ማቅረብ አለባቸው፡፡ 
  3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ኦሎምፒያ ዝቅ ብሎ፣ ከጌቱ ኮሜርሽያል ህንፃ ከፍ ብሎ ከሚገኘው የኮንስትራክሽን ሥራዎች ቁጥጥር ባለሥልጣን የግዥ ቡድን ቢሮ 4ኛፎቅ የማይመለስ ብር 100.00(አንድ መቶ) በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡ 
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለእያንዳንዱ ምድብ/ሎት/ ብር 5,000 (አምስት ሺ) በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተመሰከረለት የክፍያ ማዘዣ (CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ጥሬ ገንዘብ ማስያዝ የሚቻለው ጨረታው ከሚከፈትበት አንድ ቀን ቀደም ብሎ ባለው ጊዜ ብቻ ነው 
  5. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ አየር ላይ ክፍት ሆኖ በሚቆይበት ለ15 ተከታታይ ቀናት በሚኒስቴር መ/ቤቱ 4ኛ ፎቅ ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡ 
  6. ተጫራቾች አማራጭ ዕቃና አማራጭ ዋጋ ማቅረብ አይኖርባቸውም፡፡ 
  7. ተጫራቾች በጨረታ ሠነዱ ክፍል 6/ስድስት/ ውስጥ በሚገኘው የፍላጎት መግለጫ ላይ ለተጠየቁባቸው የቢሮ መገልገያ ዕቃዎች ዝርዝር መግለጫውን በትክክል ማሟላት ይጠበቅባቸዋል። 
  8. ጨረታው በ15ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከቀኑ 8፡30 በመ/ቤቱ 4ኛ ፎቅ ግዥ ቡድን ቢሮ ውስጥ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የመንግሥት ሥራ የማይኖርበት ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት ይከፈታል፡፡ 
  9. የባለሥልጣን መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው፡፡ 

የኮንስትራክሽን ሥራዎች ቁጥጥር ባስሥልጣን 

ግዥና ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት, 4ኛ ፎቅ 

የቢሮ ስልክ 0115-57-4158/ ፋክስ፡-0115541268/ , 

ፖ.ሣ.ቁ 24134/1000 

አድራሻ:- ግዥ ቡድን , 4ኛ ፎቅ F-04-009, 01151533-57 

ሸዋ ዳቦ ፊት ለፊት፣ ከኦሎምፒያ ዝቅ ብሎ ከጌቱ 

ኮሜርሽያል ህንፃ ከፍ ብሎ

አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ