በአራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር የመሀል ግንፍሌ የመጀ/ደ/ት/ቤት ለ2012 ዓም በጀት ዓመት እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት እና ኔትወርክ ዝርጋታ ማሰራት ይፈልጋል

በአራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር የመሀል ግንፍሌ የመጀ/ደ/ት/ቤት ለ2012 ዓም በጀት ዓመት እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት እና ኔትወርክ ዝርጋታ ማሰራት ይፈልጋል

የማስታወቂያ ቁጥር 03/2012 ዓ.ም 

በአራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር የመሀል ግንፍሌ የመጀ/ደ/ት/ቤት ለ2012 ዓም በጀት ዓመት እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት እና ኔትወርክ ዝርጋታ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ የሚገዛው ዕቃ/ተዛማጅ አገልግሎት

 • የስፖርት ቱታ የሴት የአገር ውስጥ፣
 • የስፖርት ሸራ ጫማ የሴት የአገር ውስጥ፣
 • የወረቀት ማስደገፊያ፣
 • የወረቀት መቁረጫ/ከተር/ ኤ4፣
 • የእጅ ባትሪ በቻርጅ የሚሰራ፣
 • የከለር ፕሪንተር ቀለም TK 5140፣
 • የፕሪንተር ቀለም 410A፣ ላፕቶፕ፣ ዳስከቶፕ ኮምፒዩውተር እና
 • መሰላል የብረት አወዳድሮ በግልፅ ጨረታ ሙግዛት እና የኔትወርክ ዝርጋታ ማሰራት ይፈልጋል:: 

ተጫራቾች የሚከተሉትን ቅደመ ሁኔታዎች ማሟላት ይገባቸዋል፡-

 1. በተሰማሩበት የስራ መስክ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ በአቅራቢ ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ እና ተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ የሚያቀርቡ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡ 
 2. በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ባዘጋጀው የእቃ አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ለመመዝገባቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡ 
 3. የኔትወርክ ዝርጋታ በተመለከተ በዘርፉ ስራ ላይ የተሰማሩ መሆኑን የሚያሳይ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ አለባቸው፡፡ 
 4. በኔትወርክ ዝርጋታ የሚወዳደሩ ተጫራቶች ጥሬ እቃውን ገዝተው ማቅረብ አለባቸው፡፡ 
 5. በኔትወርክ ዝርጋታ ስራ ላይ የሚወዳደሩ ተጫራቾች የምናወዳድረው ጠቅላላ የእቃ ዋጋ ከነቫቱ እና ጠቅላላ የእጅ ዋጋ ከነቫቱ በድምሩ ነው፡፡ 
 6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ የተመሰከረለት CPO 2% ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ 
 7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በማየትና ናሙና የሚቀርብባቸውን እቃዎች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ 
 8. ጨረታውን የሚያሸንፈው ድርጅት ዕቃዎቹን እስከ ት/ቤቱ ማድረስ አለበት፡፡ 
 9. ጨረታው አየር ላይ የሚቆይበት ጊዜ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 (አስር) ተከታታይ የሥራ ቀናት ይሆንና በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ 4፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡ 
 10. በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁተቋማትራሳቸው አምርተውለገበያ በሚያቀርቡት ዕቃ ወይም እሴት ጨምረው ለሚያመርቱት ምርት ካልሆነ በስተቀር የተዘጋጁ እቃዎችን ገዝተው ለሚወዳደሩበት እንደ ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነድ መግዛትና የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡ 
 11. ተጫራቾች ስርዝ ድልዝ፣ የማይነበብ ሰነድ፣ የዘገየ ሰነድ ፣ጨረታ ላይ ያልተነበበ  የዋጋ ማቅረቢያ ተቀባይነት አይኖረውም 
 12. አሸናፊ ተጫራች 10% የውል ማስከበሪያ ማስያዝ አለባቸው፡፡ 
 13. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር የያዘውን ሰነድ የማይመለስ 50 ብር /ሃምሳ ብር/ በመከፈል መግዛት ይችላሉ፡፡ 
 14. ጨረታው በማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት የጨረታውን ሰነድ ኦርጅናልና ፎቶኮፒ ቫትን ጨምሮ ተሟልቶ ለየብቻው ፖስታ ታሽጎ ሲፒኦ በፎቶ ኮፒ ውስጥ በማድረግ ቢሮ ቁጥር 3 በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የተገዛው የጨረታ ሠነድ ሙሉ በሙሉ በተጫራቾች ዋጋው ተሞልቶ በዮፁ ተፈርሞበት መግባት አለበት፡፡ 
 15. መሥሪያ ቤቱ ለግዢው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ 
 • አድራሻ፡- አራት ኪሎ አለ የስነጥበብና ዲዛይን ት/ቤት ወይም አዲስ የእናቶችና ህፃናት ሆስፒታል አጠገብ 
 • ስልክ ቁጥር፡- 011 123 28 40 / 011 154 39 55/011 154 45 31 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ። 

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ 

በአራዳ ክ/ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት የመሀል ግንፍሌ የመጀ/ደ/ት/ቤት