በባሶና ወራና ወረዳ በጉዶ በረት 1ኛ ደረጃ ት/ቤት 2ኛ ዙር የመጫወቻ ሜዳ ግንባታ ሥራ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡

የግንባታ ጨረታ ማስታወቂያ

ተስፋ ብርሃን ህፃናትና ቤተሰብ ልማት ድርጅት የተለያዩ የልማት ሥራዎችን ከቻይልድ ፈንድ ኢትዮጲያ ጋር በአጋርነት የሚሰራ አገር በቀል የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት ነው፡፡ድርጅቱ በ2012 በጀት ዓመት፡-

1)በባሶና ወራና ወረዳ በጉዶ በረት 1ኛ ደረጃ ት/ቤት 2ኛ ዙር የመጫወቻ ሜዳ ግንባታ ሥራ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም ከዚህ በታች የተመለከተውን መስፈርት የምታሟሉ ተቋራጮች እንድትወዳደሩ ይጋብዛል፡፡

ሀ.የህንፃ ግንባታ ደረጃ 7 እና በላይ ፍቃድ ያላቸው ሆኖ

ለ.የቫት ተመዝጋቢ የሆነ

ሐ.የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለው

መ.የታደሰ ፈቃድ ማቅረብ የሚችል

ሰ.የመልካም ሥራ አፈፃፀም ማቅረብ የሚችሉ ይህ ማስታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 ቀናት ውስጥ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 (መቶ ብር) ብቻ በመግዛት ሰነዱን ከቢሮ በመውሰድ በዝርዝሩ መሰረት ዋጋ በመሙላት ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0934713721/0911312718 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

ማሳሰቢያ፡-

     ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ በጨረታው አይገደድም፡፡

     ተጫራቾች የሚያቀርቧቸውን ሥራዎች ዝርዝር በአጠቃላይ ዋጋ ከነቫቱ 1 በመቶ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተመሰከረለት ሲፒኦ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

     ጨረታው በ11ኛው የሥራ ቀን በ4፡00 ሰአት ተዘግቶ በ4፡30 ላይ ይከፈታል፡፡

ጨረታው የሚገባበት አድራሻ

ለተስፋ ብርሃን ህፃናትና ቤተሰብ ልማት ድርጅት

ሰሜን ሸዋ ዞን ባሶና ወራና ወረዳ

ቀይት (ከደብረ ብርሃን ወደ ደሴ በሚወስደው መንገድ 17 ኪ.ሜ ርቀት ላይ)