ራስ ሆቴል በግቢው ውስጥ የሚገኘውን ባለአንድ ፎቅ ሕንፃ፣ በዋናው የሆቴሉ ሕንፃ ላይና ምድር ቤት በክፍትነት የሚገኙ ለቢሮነት ወይም ከሆቴሉ መደበኛ ሥራ ጋር ተመሣሣይ ላልሆነ የንግድ ሥራ አገልግሎት የሚውሉ ክፍሎችን፣ በኪራይ ለመያዝ ለሚፈልጉ ድርጅቶች/ግለሰቦች፣ ማከራየት ይፈልጋል፡፡

ለቢሮነትና ለሌሎች ሥራዎች የሚውሉ

ክፍሎችን ለማከራየት

ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ ማስታወቂያ

ራስ ሆቴል በግቢው ውስጥ የሚገኘውን ባለአንድ ፎቅ ሕንፃ፣ በዋናው የሆቴሉ ሕንፃ ላይና ምድር ቤት በክፍትነት የሚገኙ ለቢሮነት ወይም ከሆቴሉ መደበኛ ሥራ ጋር ተመሣሣይ ላልሆነ የንግድ ሥራ አገልግሎት የሚውሉ ክፍሎችን፣ በኪራይ ለመያዝ ለሚፈልጉ ድርጅቶች/ግለሰቦች፣ ማከራየት ይፈልጋል፡፡

ስለጨረታው በዝርዝር የሚያስረዳውን የጨረታ ሰነድ ከሆቴሉ ዋና ሥራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ብር 100.00(አንድ መቶ) ከፍለው መግዛት ይችላሉ፡፡

ለመከራየት የሚፈልጉ ድርጅቶች/ግለሰቦች በሆቴሉ ተገኝተው ለኪራይ የተዘጋጁትን ክፍሎች መመልከት ይችላሉ፡፡ ተከራዮች ክፍሎቹን ከተመለከቱ በኋላ ለኪራይ የመረጡትን ክፍል/ክፍሎች፣ በካሬ ሜትር ከጨረታ መነሻው ዋጋ በላይ ምን ያህል እንደሚከፍሉ በመግለፅ፣ የኪራይ ዋጋቸውን በጽሁፍ ለዚሁ በተዘጋጀው ቅፅ ሞልተው በጨረታው ሳጥን ውስጥ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር ሰባት የሥራ ቀናት ውስጥ እንዲያስገቡ ይጠበቅባቸዋል፡፡

ጨረታው፣ መገኘት የፈለጉ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት በተከታዩ የሥራ ቀን ከጧቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡

ስለሚከራዩት ክፍሎች ተጨማሪ መግለጫ የሚፈልጉ ድርጅቶች/ግለሰቦች ወደ ሆቴሉ ሥራ አስኪያጅ ጽ/ቤት በግንባር በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥሮች 0115517060 Ext.440 /0115549014 በመጠቀም ማግኘት ይችላሉ፡፡

ሆቴሉ በማንኛውም ምክንያት ከላይ የተገለፀውን የኪራይ አፈጻጸም ለመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

                ራስ ሆቴል