የጨረታ ማስታወቂያ፡-
የጨረታ ቁጥር DCE/SHE/017/2012
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ በሸጎሌ መኖሪያ አፓርትመንት (16-08B) ፕሮጀክት ስራ አገልግሎት የሚውሉ ANGEL IRON 40X40X3MM እና PRE COLORE CONCRETE TILE 300X300X30MM ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም፡-
- ተጫራቾች ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ለተጨማሪ
እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚያቀርቡት ገንዘብ በተጫራቾች መመሪያ
ተራ ቁጥር 7.3 እና 7.4 በተጠቀሰው መሠረት መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) በመክፈል ዘወትር በስራ ሰአት ቅዳሜን ጨምሮ ባሉት 07 ተከታታይ የሰራ ቀናት ጃንሜዳ አዣዥነትና ስታፍ ኮሌጅ (17-06B) ፕሮጀክት ግቢ ውስጥ በሚገኘው የፕሮጀክት ገንዘብ ያዥ ቢሮ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች ካታሎግ ፣ ናሙናና የጥራት ማረጋገጫ
(Quality Certificate) ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ወይም በጨረታ መክፈቻ ቀን
በካታሎጉ ላይ የሚወዳደሩበትን ዕቃ ለይቶ በማመልከት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቧቸው ዕቃዎች በተጠቀሰው ብዛት (Quantity) መሠረት መሆን
ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ እስከ ሚያዝያ 30/2012 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ሚያዝያ 30/2012 ዓ/ም ከቀኑ 8፡30 ከሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ
ወኪሎቻቸው በተገኙበት በፕሮጀክቱ ቢሮ ይከፈታል፡፡
- ፕሮጀክቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ
የጃንሜዳ አዣዥነትና ስታፍ ኮሌጅ ፕሮጀክት (17-06B)
የቀጥታ ስልክ ቁጥር ዐ118-95-98-10 0934560631-
6 ኪሎ(ወደ ፈረንሳይ ቤላ መንገድ መሄጃ)የሚገኘው የመከላከያ አዣዥነትና ስታፍ ኮሌጅ ካንፕ ውስጥ