ኤደን ቢዝነስ አክሲዮን ማህበር ጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ አገና ከተማ እና ቸሀ ወረዳ በሚገኘው የኤደን ግብርና ፕሮጀክት ቅጥር ግቢ ውስጥ እንዲሁም ሳርቤት አካባቢ ዕድገት ድርና ማግ ፋብሪካ ቅጥር ግቢ ውስጥ በሚገኘው በአክሲዮን ማህበሩ መጋዘን ውስጥ የሚገኙተን፡- በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ የፈልጋል፡፡

የሸያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

ኤደን ቢዝነስ አክሲዮን ማህበር ጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ አገና ከተማ እና ቸሀ ወረዳ በሚገኘው የኤደን ግብርና ፕሮጀክት ቅጥር ግቢ ውስጥ እንዲሁም ሳርቤት አካባቢ ዕድገት ድርና ማግ ፋብሪካ ቅጥር ግቢ ውስጥ በሚገኘው በአክሲዮን ማህበሩ መጋዘን ውስጥ የሚገኙተን፡-

 1. አንድ ጃክ ቫን የጭነት መኪና፤
 2. የተለያዩ ያገለገሉ ካርትሪጆችን፤
 3. ልዩ ልዩ ያገለገሉ የመኪና ጎማዎች፤
 4. ሁለት ያገለገሉ የውሀ መሳቢያ ፓምፕች፤
 5. የማዳበሪያ ጆንያዎች / PP Bags/፤
 6. ቁርጥራጭ ብረታብረቶች እና እንጨቶች በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ የፈልጋል፡፡

ማሳሰቢያ

 1. ተጫራቾች ለሽያጭ የተዘጋጁትን ዕቃዎች በቦታው ተገኝቶ በማየትና ለጠቅላላው ዋጋ በመሙላት በጨረታው ላይ መወዳደር ይችላሉ፡፡
 2. በዚህ የሽያጭ ጨረታ ላይ ለመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ግለሰብም ሆነ ድርጅት የጨረታ ማስከበሪያ 10,000.00(አስር ሺህ ብር )በሲፒኦ ብቻ በማስያዝ አንድ ወይም ከአንድ በላይ የሆኑ ዕቃዎችን ለመግዛት መወዳደር ይችላል፡፡
 3. በዚህ ጨረታ ላይ የሚሳተፉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 50 (ሀምሳ ብር) በመክፈል ከአ/ማህበሩ ጽ/ቤት EGST ህንፃ 5ኛ ፎቅ ቢሮ 503 ማግኘት ይችላሉ፡፡ 
 4. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የሚጫረቱበትን ዋጋ የያዘ ፖስታ ይዘው በመቅረብ ከሰኞ እስከ አርብ ዘወትር በስራ ሠዓት እንዲሁም ቅዳሜ ግማሽ ቀን እስከ ቀኑ 6፡00 ሠዓት ድረስ በአክሲዮን ማህበሩ ዋና  ፅ/ቤት በሚገኝበት ሳር ቤት አካባቢ EGST ህንፃ 5ኛ ፎቅ ቢሮ 503 ለዚሁ ሲባል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይችላሉ፡፡ ጨረታው በ10ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ቀን ልክ 4፡30 ይከፈታል፡፡
 5. ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው፡፡

ለተጨማሪ መረጃ

በስልክ ቁጥር 0113-691014/0113-691457 ይደውሉልን

ልናስተናግድዎት ዝግጁ ነን፡፡