የጨረታ ማስታወቂያ
ለመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ኢንሳ 11-08B ፕሮጀክት አገልግሎት የሚውል Greenery work (ምድረ ግቢ ማስዋብ) ሥራ ለመስራት ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
- ተጫራቾች ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚያቀርቡት ገንዘብ በተጫራቾች መመሪያ ተራ ቁጥር 7.3 እና 7.4 በተጠቀሰው መሠረት መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት ወሎ ሰፈር አይቤክስ ሆቴል አካባቢ በሚገኘው ፕሮጀክት ግብአት አቅርቦትና አስተዳደር ቢሮ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ዋጋ በመሙላታቸው በፊት ሳይቱን በአካል ቀርበው መመልከት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቧቸው ዕቃዎች በተጠቀሰው ብዛት (Quantity) መሠረት መሆን ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ እስከ ሚያዚያ 16/2012 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ሚያዚያ 16/2012 በጠዋቱ 4፡15 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
- ፕሮጀክቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- የመከላከያ ኮንስትራክሽ ኢንተርፕራይዝ ኢንሳ 11-08 ፕሮጀክት
የቀጥታ ስልክ ቁጥር 0118-40-28-07
ወሎ ሰፈር አይቤክስ ሆቴል አጠገብ