በኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት ድርጅታችን በ6 ወራት ውስጥ የሚያሰራጨውን ስኳር በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማጓጓዝ ይፈልጋል፡፡

በኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት

የኢንዱስትሪ ውጤቶች ግዥ ዳይሬክቶሬት

የጭነት አገልግሎት ግዥ 

ጨረታ ማስታወቂያ (ቁጥር 010/2012)

 

 

ድርጅታችን በ6 ወራት ውስጥ የሚያሰራጨውን ስኳር በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማጓጓዝ ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ፤

 

  1. በዘርፉ የታደሰ ንግድ ሥራ ፍቃድ (ለግል ድርጅቶች)፣ የብቃት ማረጋገጫ እና የግብር ከፋይነት ምዝገባ ሠርተፍኬት ያላቸው አጓጓዥ ድርጅቶች በሙሉ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡
  2. ተጫራቾች ለጨረታው የተዘጋጀውን ዝርዝር የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ፒያሳ ቢስ መብራት አካባቢ ከሚገኘው የድርጅቱ ዋና መስርያ ቤት የኢንዱስትሪ ውጤቶች ግዥ ዳይሬክቶሬት የምግብና ጠቅላላ ሸቀጣ ሸቀጥ ቡድን ቢሮ በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 100,000.00 (በሲ.ፒ.ኦ ብቻ) ለብቻው በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ መወዳደሪያ ዋጋቸውንና ከላይ በተራ ቁጥር 1 የተጠቀሱ ህጋዊ ሠነዶችን (ኦሪጅናል እና ኮፒ) ለየብቻው በታሸገ ኤንቨሎፕ እስከ ሚያዝያ 2 ቀን 2012 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ ይችላሉ፡፡
  5. ጨረታው በተመሳሳይ ሚያዝያ 2 ቀን 2012 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  6. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 

የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት

 

ስልክ ቁጥር 0113692439/0113692711

www.eiide.com.et