የጨረታ ማስታወቂያ፡-
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ በአዲስ አበባ ከተማ ለሚያስገነባው ኢንሳ ፕሮጀክት11-08B Epoxy floor Work ተጫራቶችን በግልፅ ጨረታ ማወዳደር ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም፡-
- ተጫራቾች ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚያቀርቡት ገንዘብ በተጫራቾች መመሪያ ተራ ቁጥር 7.3 እና 7.4 በተጠቀሰው መሠረት መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቾች ፋይናንሻል ሪፖርት ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን ይኸውም ዓመታዊአፈፃፀማቸው (Annual turnover) ቢያንስ 5,000,000 (አምስት ሚሊዮን ብር) መሆን ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች አምራች፣ አቅራቢ እንዲሁም አገልግሎት ሰጪ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት ወሎ ሰፈር አይቤክስ ሆቴል አካባቢ በሚገኘው ፕሮጀክት ግብአት አቅርቦትና አስተዳደር ቢሮ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ እስከ ሚያዚያ 6/2012 ዓ.ም ከጥዋቱ 4፡ዐዐ ሰዓት ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ሚያዚያ 6/2012 ከጠዋቱ 4፡15 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
- ፕሮጀክቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡–የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ኢንሳ ፕሮጀክት 11-08B
የቀጥታ ስልክ ቁጥር ዐ118-4ዐ-28-07
ወሎ ሰፈር አይቤክስ ሆቴል አጠገብ