ሬድ ሲ ትሬዲንግ ኃ.የተ.የግ. ማህበር በሥሩ የሚገኙ 2 የኘሮከለር ፎቶና ቪዲዮ የድርጅቱን ቅርንጫፍ በተናጠል ወይም በጠቅላላ አጫርቶ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

የጨረታ ማስታወቂያ

  1. ሬድ ሲ ትሬዲንግ ኃ.የተ.የግ. ማህበር በሥሩ የሚገኙ 2 የኘሮከለር ፎቶና ቪዲዮ ቅርንጫፎቹ፡-

 

ሀ/   ቦሌ ሚካኤል  ቦሌ ክ/ከተማ ቀበሌ 01 የቤት ቁጥር 5057 ቢሮ ቁጥር 1-01 ፍቅር ካፌ ህንፃ ላይ፤

 

ለ/   አያት የካ ክ/ከተማ ወረዳ 13 የቤት ቁጥር አዲስ የቢሮ ቁጥር M-008 ጌት ህንፃ ላይ፤

የድርጅቱን ቅርንጫፍ በተናጠል ወይም በጠቅላላ አጫርቶ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

 

ተጫራቾች ሊያሟሉ የሚገባቸው፡-

  1. በእያንዳንዱ ቅርንጫፍ የሚገኙትን ፎቶ ቤቶችና የፎቶ ግራፍ እቃዎችን፣ የፍቶ ማተሚያ ማሽኖችና እቃዎችን በአሉበት ሁኔታ መግዛት የሚችሉ፣

 

  1. የጨረታ ማስከበሪያ በድርጅቱ ስም ሲፒኦ ብር 50,000 (ሃምሳ ሺህ) ማስያዝ የሚችል፣
  2. የጨረታ ሰነዱን ከላይ ከሀ – ለ የተጠቀሱት የፎቶ ቤት አድራሻ ብር 50.00 (አምሣ ብር) እየከፈላችሁ መግዛት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

 

  1. መኪኖች፣

ተ.ቁ

የመኪናው ዓይነት

የተሰራበት ሀገር

ሞዴል

የተሰራበት ዘመን

1.

ሊፋን (Lifan)

ቻይና

X-60 SUV

2012 እ.ኤ.አ

2.

ዳማስ (Damas)

ደው (ኮሪያ)

VanY711

1999  

 

ዝርዝር ሁኔታውን በ0911-230654 ወይም /0912-021110/ በመደወል መረዳት የሚቻል ሲሆን፣ በተራ ቁጥር ሀ እና ለ በየቅርንጫፎች በመገኘትም ያሉትን ማሽኖች፣ የተሟሉ እስቱዲዮችን፣ እና አጠቃላዩን ሁኔታ መጎብኘት ይቻላል፡፡ በተጨማሪም የፎቶ ህትመት ማሽን ብቻ መግዛት ለሚፈልግ  በመገናኛ ቅርንጫፍ 570 Fuji Frontier ያለ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

 

ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ከመጋቢት 21-28 ቀን 2012 ዓ.ም እስከ 4፡00 ድረስ ድረስ ተጫራቾች በዋና መ/ቤታችን በ22 ማዞሪያ ጎላጎል ታወር ጀርባ ከኪያ ሜድ ኮሌጅ ቀጥሎ ባለው ሕንፃ በ1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 1-01 ቀርበው በተዘጋጀው ሳጥን የሚጫረቱበትን ሰነድ በታሸገ ኤንቨሎፕ አድርገው ማስገባት የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን፤

 

ጨረታው መጋቢት 28 ቀን 2012 ዓ.ም ከቀኑ 5 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት መሆኑን እናስታውቃለን፡፡ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ከአገኘ በጨረታው አይገደድም፡፡

 

ሬድ ሲ ትሬዲንግ ኃ.የተ.የግል ማህበር

* የሲፒኦ አድራሻ ሬድ ሲ ትሬዲንግ ኃ.የተ.የግል ማህበር ወይም (Red Sea Trading PLC)