በሞሐ ለስላሳ መጠጦች ኢንዱስትሪ አ.ማ. ንፋስ ስልክ ፔፕሲ ኮላ ፋብሪካ ያገለገለ ተሳቢ ተሽከርካሪ ባለበት ሁኔታ በዝግ ጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

የጨረታ ማስታወቂያ

በሞሐ ለስላሳ መጠጦች ኢንዱስትሪ አ.ማ. ንፋስ ስልክ ፔፕሲ ኮላ ፋብሪካ ያገለገለ ተሳቢ ተሽከርካሪ ባለበት ሁኔታ በዝግ ጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም ተጫራቾች የጨረታውን ሠነድ በፋብሪካው የግዥና ክምችት መምሪያ በመቅረብ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ) እየከፈሉ ከወሰዱ በኋላ ተሽከርካሪውን በመመልከት የሚገዙበትን ዋጋ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 (ሰባት) ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ በፋብሪካው የግዥና ክምችት መምሪያ በማቅረብ መወዳደር ይችላሉ፡፡

ጨረታው በ8 (ስምንተኛው) የሥራ ቀን ከጥዋቱ በ4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡

  • የጨረታ ዋስትና ብር 10,000.00 (አሥር ሺ ብር) በባንክ በተመሰከረለት ሲ.ፒ.ኦ ማስያዝ አለባቸው፣
  • የመጫረቻ ዋጋ አንተርሶ ማቅረብ አይቻልም፣
  • የጨረታ አሸናፊ የመልካም ሥራ አፈጻጸም ዋስትና ማስከበሪያ በመያዣነት የጠቅላላ ዋጋውን 10% በቅድሚያ ማስያዝ ይኖርበታል፣
  • ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ በጨረታው አይገደድም፡፡

ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 0114-65-43-78

ግዥና ክምችት መምሪያ ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡