< Back
በን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ወረዳ 11 ጤና ጣቢያ የጄኔሬተር ግዥ፣የመድሃኒቶች ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር፡– 03
በን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ወረዳ 11 ጤና ጣቢያ በ2012 በጀት ዓመት የ3ኛ ዙር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
- ሎት1. የጄኔሬተር ግዥ
- ሎት2. የመድሃኒቶች ግዥ
ከላይ የተዘረዘሩ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ህጋዊ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ እንድትጫረቱ ይጋብዛል፡፡
- ተጫራቾች በምትሳተፉበት የግዥ አይነት በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና የንግድ ምዝገባ ወረቀትና የአቅራቢነት ሰርተፍኬት ኮፒ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢነትና ግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ማስረጃ ኮፒ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የዘመኑን ግብር ስለመክፈላቸው የግብር ከፋይ መለያ (ቲን ነምበር) እና ታክስ ክሊራንስ ሰርተፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለሚወዳደሩበት ለአንደኛ ሎት ብር 5,000 (አምስት ሺህ ብር) ለሁለተኛ ሎት ብር 3,000 (ሶስት ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ብቻ ከኦርጅናል ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት በማዕከሉ የፋይናንስ እና ክፍያ ቡድን መሪ ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ክፍል በሚገባ በመሙላት ሁሉም ሰነድ ላይ የድርጃታችሁን ማህተምና ዋጋ መሙያው ላይ በመፈረም ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት የፋይናንስ እና ክፍያ ቡድን መሪ ቢሮ ቁጥር 43 ለዚህ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታሳጥኑ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ እለት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 4ኛ ፎቅ ጤና ጣቢያው አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል፡፡
- የቀረበው ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆኑና አለመሆኑ ካልተገለጸ የቀረበው ዋጋ ቫትን እንዳካተተ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡
- ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ናሙና የማቅረብ ግዴታ የሚጠበቅባቸው ሆኖ እቃዎቹን ሲያስገቡ ወዲያውኑ ናሙና ተመላሽ ይሆናል፡፡
- ከጨረታው ሰነድ የዋጋ መሙያ ውጪ ተሞልቶ የሚመጣ የዋጋ መሙያ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
- ተጫራቹ በሌሎች ተጫራቶች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋመስጠትም ሆነ ጨረታውን ማዛባት ከጨረታው ውጪ ያደርጋል፡፡
- ጥቃቅንና አነስተኛ የሆናችሁ ተጫራቶች በጨረታው ለመሳተፍ ከኣደራጃችሁ የመንግስት ተቋም በአድራሻችን የተፃፈ ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው:
አድራሻ፡ ን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ወረዳ 11 ጤና ጣቢያ ልዩ ስሙ ሀና ማሪያም
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0118116335 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ጤና ጽ/ቤት
የወረዳ 11 ጤና ጣቢያ