የኦዲት ጨረታ ማስታወቂያ
ፕሮጀክት ሐረር ኢትዮጵያ መንግስታዊ ያልሆነ ለትርፍ ያልተቋቋመ የሐገር በቀል በጎ አድራጎት ድርጅት ሲሆን መንግስት ባወጣው የዳግም ምዝገባ ሥርአት አጠናቆ በሰርተፊኬት ቁጥር 2873 በመመዝገብ በመላው ኢትዮጵያ በበጎ አድራጎት ስራ ላይ እንዲንቀሳቀስ የተፈቀደለት ድርጅት ነው፡፡
በመሆኑም ፕሮጀክት ሐረር ኢትዮጵያ የ 2019 በጀት አመት ሂሳብ ኦዲት ማስደረግ ይፈልጋል፡፡ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡
1.በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
2.በተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
3.በ “IPSAS”ኦዲት ሰርቶ የሚያውቅ፡፡
4.ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ 5 (አምስት) የስራ ቀናት ውስጥ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በዋናው መስሪያ ቤት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
5.ጨረታው ሰኞ መጋቢት 7 ቀን 2012 ዓ.ም (March 16, 2020 G.C) ከጠዋቱ 4፡00 ተዘግቶ በዚያኑ ቀን 4፡30 ላይ ይከፈታል፡፡
አድራሻ፡-ጉርድ ሾላ ሰአሊተ ምህረት ቤተ ክርስቲያን ፊትለፊት ቸሻየር ሰርቪስ ኢትዮጵያ ህንፃ ላይ 5ኛ ፎቅ
ስልክ ቁጥር ፡-0911815672, 0913700200