ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር 01/2013
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በምዕራብ ጎጃም ዞን አስተዳደር ፍ/ ሠላም ከተማ አስተዳደር የከተማ ልማት ቤቶች ኮንትራክሽን አገልግሎት ጽ/ቤት በUIIDP በጀት
- ሎት– 01 ኤሌከትሮኒክስና ተዛማጅ ዕቃዎች
- ሎት 02 የጽዳት ዕቃ
- ሎት03 የጽህፈት መሣሪያዎች እና
- ሎት 04 የተዘጋጁ የፈርኒቸር ውጤቶችን እንዲሁም በመደበኛ በጀት
- ሎት 5 የውሃ ታንከር /ሮቶ/ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች ፣ መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ያጋብዛል፣
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው
- የግዥው መጠን ብር 200.000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋገጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚገዙ የዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል
- የተሞላው ዋጋ ማንኛውንም ግብር ወይም ታክስ ያካተተ መሆን አለበት
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያና ዋስትና ቢድ ቦንድ ለሚወዳደሩበት ብር ለሎት 01, 8,540 /ስምንት ሺህ አምስት መቶ አርባ ብር/ ለሎት 02 110 /አንድ መቶ አስር ብር/ ለሎት 03 3000 /ሶስት ሺህ ብር / ለሎት 04 1,500 /አንድ ሺህ አምስት መቶ ብር/ ለሎት 05 1,300 / አንድ ሺህ ሶስት መቶ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ የጨረታ ማስከበሪያ አገልግሎት ማስያዝ አለባቸው
- ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወጥ በሆኑ እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያ በተለየ ፖስታ ሰጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ስምና አድራሻ በማስቀመጥ በከተማ ልማት ቤቶች ኮንስትራከሽን አገልግሎት ጽ/ቤት በግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ደጋፊ ቡድን ወይም ቢሮ ቁጥር 22 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ለ15 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ይውልና 16ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ የጨረታ ሰነዱን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ደጋፊ ቡድን ክፍል በቢሮ ቁጥር 22 ጨረታው ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ይቆይና በ16ኛው ቀን ማለትም በ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ይከፈታል ባይገኙም ጨረታውን ለመከፈት አያስተጓጉልም፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቧቸውን ዕቃዎች በፍ/ሰላም ከተማ አስተዳደር ግቢ ውስጥ ካለው ንብረት ክፍል አምጥተው የሚያስረክቡ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ዋጋቸውን ሲሞሉ የጨረታ ሰነዱ በሚያስቀምጠው አይነትና ዝርዝር መግለጫ መሰረት ብቻ ተሞልቶ መቅረብ አለበት፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ፍ/ሰላም ከተማ አስተዳደር ከተማ ልማት ቤቶችና ኮንስትራክሽን አገልግሎት ጽ/ቤት የግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ደጋፊ ቡድን ቢሮ ቁጥር 21 ከዋና ገንዘብ ያዥ እጅ የማይመለስ ብር 50.00 /ሃምሳ ብር/ በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 22 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር ፡– 0587750346/1775/0339 በመደወል ማግኘት ይችላሉ
- ከላይ ስለ ጨረታው ያልተገለፀ ነገሮች ቢኖሩ በየግዥ አፈፃፀም መመሪያ ቁጥር 1/2003 መሰረት ተፈፃሚ ይሆናሉ፡፡
የፍኖተ ሠላም ከተማ አስተዳደር ከተማ ልማት
ቤቶችና ኮንስትራክሽን አገልግሎት ጽ/ቤት የግዥ
ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን