የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 016/2012
ፀሐይ ኢንዱስትሪ አ.ማ ቃሲቲ ብረታ ብረት ፋብሪካ በአዳማ ከተማ ለሚያሰራው የመጋዘን ግንባታ ስራ ደረጃ 5 እና ከዚያ በላይ የሆነ የሕንፃ ስራ ተቋራጮችን በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል:: ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶ የምታሟሉ የስራ ተቋራጮች በጨረታው እንድትሳተፉ ይጋብዛል::
- የግንባታ ስራ ፍቃድ ደረጃቸው 5 እና ከዚያ በላይ የሆኑ::
- ተጫራቾች በመስኩ የታደሰ እና ሕጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው በሚመለከተው መ/ቤት የተመዘገቡበት የምዝገባ የምስክት ወረቀት እና የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ እንዲሁም ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡ መሆን አለባቸው::
- ተጫራቾች ለዚሁ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ቃሊቲ መናኸሪያ አካባቢ ፣ ከቶታል ነዳጅ ማደያ ፊት ለፊት ፣ ከካፍደም ሲኒማ በኩል 700 ሜትር ገባ ብሎ በሚገኘው ከፋብሪካው የግዥ ዋና ክፍል የማይመለስ ብር 50.በመክፈል መውሰድ ይችላሉ::
- የጨረታው ተሳታፊዎች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ፋይናንሺል እና ቴክኒካል በሚል ተለይቶ ለየብቻው አንድ ኦርጅናል እና አንድ ኮፒ በታሸገ ፖስታ በማድረግ በፋብሪካው ግዢ ዋና ክፍል ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል::
- ጨረታው ሐምሌ 07 ቀን 2012 ዓ.ም 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በእለቱ በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል::
- ፋብሪካው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ፀሐይ ኢንዱስትሪ አ.ማ
ቃሊቲ ብረታ ብረት ፋብሪካ
ዋና መ/ቤት ስልክ 011-4-34-01-10/011-4-34-40-06