የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 015/2012
ፀሐይ ኢንዱስትሪ ኢማ ቃሊቲ ብረታ ብረት ፋብሪካ
- ልዩ ልዩ ቤሪንጎችን ፣
- የቆዳ የእጅ ጓንቶችን ፣
- የፕሪንተር ቶነሮችን እና ቦክስ ፋይሎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል::
በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች ስለ ጨረታው የተዘጋጅውን ዝርዝር መግለጫ ዘወትር በሥራ ሰዓት ጨረታው በማስታወቂያ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ እስከ ሰኔ 23/2012 ዓ.ም 4፡00 ሰዓት ድረስ በፋብሪካው የግዢ ዋና ክፍል ቢሮ በመምጣት የማይመለስ ብር 50 / ሀምሳ/ በመክፈል መውስድ ይችላሉ::
ስለሆነም:
- . ተጫራቾች በመስኩ የታደሰ እና ሕጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው እንዲሁም ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡ መሆን አለባቸው፣
- የጨረታው ተሳታፊዎች የሚያቀርቡትን የጨረታ ሰነድ በታሸገ ፖስታ በማድረግ ለፋብሪካው የግዥ ዋና ክፍል ቢሮ ለዚህ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፣
- ጨረታው ሰኔ 23/2012 ዓ.ም 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፣
- ተጫራቾች ለሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ጠቅላላ ዋጋ 2% የጨረታ ማስከበሪያ በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፣
- ፋብሪካው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ፀሐይ ኢንዱስትሪ አ.ማ ቃሊቲ ብረታ ብረት ፋብሪካ
ዋና መ/ቤት ስልክ 011 4-34-01-10/011-4 34-40-06