የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 014/2012
ፀሐይ ኢንዱስትሪ አ.ማ ቃሊቲ ብረታ ብረት ፋብሪካ ከዚህ በታች በሁለት ሎት የተጠቀሱትን ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል::
- ሎት 1- የተለያዩ የፅህፈት መሳርያዎች፣ የቀለም ብሩሾች፣ የፕሪንተር ቀለሞች፣ የፕላስቲክ መጥረጊያ፣ አልኮል፣ ኤር ፍረሽነር እና ፊልተር ማስክ::
- ሎት 2- የተለያዩ ሄክሳጎናል ሄድ ቦልቶች፣ አለን ቦልቶች፣ ታፐር ሄድ አለን ቦልቶች፣ ሄድለስ አለን፣ ግሪስ ኒፕልስ፣ ሰርክሊፕስ ሪሙቨር (interior፣ ፔለር ሪሙቨር 1500/3 እና ኦክ ስፓነር::
በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች ስለ ጨረታው የተዘጋጅውን ዝርዝር መግለጫ ዘወትር በሥራ ሰዓት ጨረታው በማስታወቂያ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ እስከ ግንቦት 11/2012 ዓ.ም 4፡00 ሰዓት ድረስ ከፋብሪካው የግር ዋና ክፍል ቢሮ የማይመለስ ብር 50 /ሀምሳ/ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ::
ስሰሆነም:
- ተጫራቾች በመስኩ የታደሰ እና ሕጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው እንዲሁም ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡ መሆን አለባቸው፣
- የጨረታው ተሳታፊዎች የሚያቀርቡትን የጨረታ ሰነድ በታሸገ ፖስታ በማድረግ ለፋብሪካው የግዥ ዋና ክፍል ቢሮ ለዚህ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፣
- ጨረታው ግንቦት 11/2012 ዓ.ም 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፣
- ተጫራቾች ለሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ጠቅላላ ዋጋ 2% የጨረታ ማስከበሪያ በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፣
- ፋብሪካው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡
ፀሐይ ኢንዱስትሪ አ.ማ. ቃሊቲ ብረታ ብረት ፋብሪካ
ዋና መ/ቤት ስልክ 011 4-34-01-10/011-4 34-40-06