የጨረታ ማስታወቂያ
ጨፌ ኦሮሚያ ጽ/ቤት
- የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን ቋሚ ዕቃዎችን፣
- የጽዳት ዕቃዎችን፣
- የጽህፈት መሣሪያዎችን እና
- የመኪና ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ፣
ህጋዊና የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ በጨረታ ላይ ለመካፈል የሚያስችል ማስረጃ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ:- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ከጽ/ቤታችን 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 20 ለዚህ የተዘጋጀውን ዶክሜንት መግዛት ይችላሉ፣
- የሚወዳደሩበትን ዝርዝር ዋጋ በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ ማስታወቂያው ከወጣበት እስከ 16ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ አራት ሰዓት 4:00 ድረስ ለዚሁ ግዢ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፣
- የመወዳደሪያ ዋጋው ከቫት ጋር ወይም ያላ ቫት መሆኑ መገለጽ አለበት፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ኛው የሥራ ቀን በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ በ4:30 ሰዓት ላይ ይከፈታል:: 16ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ፣ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል::
- ተጫራቾች ለመወዳደር ካቀረቡት ጠቅላላ ዋጋ 2% የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ /CPO/ ከጨረታ ዶክሜንት ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ለጨረታው የሚቀርቡ ዕቃዎች ትክክለኛና (ኦሪጂናል) መሆን አለባቸው፡፡ የተመሳሰለና ትክክለኛ ያልሆነ ዕቃ ለጨረታው ቢቀርብ፣ ለጨረታው ማስከበሪያ የተያዘው ገንዘብ አይመለስም፡፡
- ተጫራቾች የጽ/መሣሪያና የጽዳት ዕቃዎችን ናሙና ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ጨረታውን ያሸነፉ ተወዳዳሪዎች አሸናፊነታቸው በደብዳቤ ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ እስከ ሰባት ቀን ድረስ ዕቃውን ገቢ ማድረግ አለባቸው፡፡ከዚህ ቀን በኋላ ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው ገንዘብ ለመንግሥት ገቢ ይሆናል፡፡
- ከዚህ በፊት ጨረታዎችን አሸንፈው ዕቃውን በወቅቱ ገቢ ማድረግ ያልቻሉና ከተራ ቁ. 1-7 የተገለጹትን ያላሟሉትን ጽ/ቤቱ ከጅምሩ ከጨረታው ውጭ ማድረግ ይችላል፡፡
- ጽ/ቤቱ ሌላ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
አድራሻ:-ሳር ቤት፣ ኣካባቢ ከኦሮሚያ ቢሮዎች ፊት ለፌት ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0113716611 መጠየቅ ይቻላል፡፡
የጨፌ ኦሮሚያ ጽ/ቤት