Construction Machinery / Construction Machinery and Equipment / Machinery and Equipment / Water Engineering Machinery and Equipment

ጢስ እሳት ውኃ ሥራዎች ኃ/የተ/የግ/ማህበር ለ2013 ዓ.ም በጀት ዓመት ለሚከናውናቸው ለመስኖ፤ መጠጥውኃ ግንባታ ፕሮጀክቶች እና ለውኃ ጉድጓድ ቁፋሮ ስራዎች ማሽነሪዎች፤ የኮንስትራክሽን መሣሪያዎች እና ተሽከርካሪዎችን በመከራየት ማሰራት ይፈልጋል

የኮንስትራክሽን መሳሪያዎች፤ተሽከርካሪዎችና ማሽነሪዎች ግልጽጨረታ ማስታወቂያ

ጢስ እሳት ውኃ ሥራዎች ኃ/የተ/የግ/ማህበር ለ2013 ዓ.ም በጀት ዓመት ለሚከናውናቸው ለመስኖ፤ መጠጥውኃ ግንባታ ፕሮጀክቶች እና ለውኃ ጉድጓድ ቁፋሮ ስራዎች የሚያስፈልጉትን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትንማሽነሪዎች፤ የኮንስትራክሽን መሣሪያዎች እና ተሽከርካሪ›ዎችን በመከራየት ማሰራት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተወዳዳሪዎች በ2012 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣የተጨማሪ እሴት ታክስናየግብር ከፋዮች የምዝገባ ሰርተፊኬትና የሚያከራዪት ማሽነሪ ወይም ተሽከርካሪዎች የባለቤትነት ማረጋገጫ ሊብሬ ኮፒውንበማያያዝ እና ለማመሳከሪያነት ኦሪጅናል ሊብሬ በመያዝ ባህር ዳር ከተማ ቀበሌ 11 (ቴዲ አሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ ፊትለፊት) በሚገኘው የኩባንያው ቢሮ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00/ሁለት መቶ ብር/ በመግዛት መሳተፍ ይችላሉ፡

 1.  የሚያስፈልጉ የተሽከርካሪዎችና የማሽነሪዎች ብዛት እንደ ፕሮጀክቶች ቁጥርና አስፈላጊነት አንጻር እየታየ የሚወሰን ይሆናል፡፡
 2. ተሸከርካሪዎችና ማሽነሪዎች የሚሰማሩት ቦታ እና በጨረታ ሰነዱ መሰረት በተገለፀው አግባብ ለግንባታ ፕሮጀክቶች፤ለጉድጓድ ቁፋሮ ስራዎች ለሱፐርቪዥና ለሰርቪስ አገልግሎት ነው፡፡
 3. የጨረታው አሸናፊ የሚወስነው በጨረታ ሰነዱ ውስጥ በተመለከቱት መስፈርቶች መሠረት ሲሆን ጨረታው ዜግነትንሳይመለከት ለማንኛውም አቅራቢ ክፍት ነው፡፡
 4. አከራዎች የጨረታ ሰነዳቸውን ለዚህ ተግባር በተዘጋጀ ሳጥንቢሮ ቁጥር 09 ገቢ የሚያደርጉበት የመጨረሻ ቀን ጥቅምት 02ቀን 2013 ዓ.ም እስከ ቀኑ 8፡00 ሰዓት ብቻ ነው፡፡
 5.  የጨረታ መክፈቻው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰአት ተዘግቶ በተመሳሳይ ሰአት ይከፈታል፡፡
 6. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ተሸከርካሪ/ማሽነሪ/ የጨረታ ማስከበሪያ ለአንድ ማሽን(ዶዘር፤አክስካቫተር፤ሎደር፤ግሬደር፤ኮምፓክተር) ብር 20,000.00 (ሀያ ሺህ ብር)፤ለቀላል ተሸከርካሪዎች (ሚኒጋቢና፤ዳብልጋቢና፤ ነጠላ ጋቢና ፤ስቴሽን ፤ የጭነት አይሱዙ፤ሚኒ ፤አውቶ ሞቢል) ብር 10,000.00 (አስር ሺህ ብር) ለከባድ ተሸከርካሪዎች(ለገልባጭ፤ለክሬን፤ለሻወር ትራክ ፤ሃቤድ እና ሎውቤድን ጨምሮ) ብር 15,000 /አስራ አምስት ሺህ ብር / እና ለመበየጃ ማሽንብር 5,000.00/አምስት ሽህ/ ብር CPO ወይም የባንክ ጋራንቲ በማሠራት ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ሣጥን ውስጥ ማስገባትየምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን በኢንሹራንስ ወይም በሌላ መልክ የሚቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
 7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00(ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት ቀበሌ (ቴዲአሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ ፊት ለፊት) በሚገኘው የኩባንያው ቢሮ ቁጥር 02 በመቅረብ በመግዛት መውሰድ ይችላሉ፡
 8. ጨረታው ጥቅምት 02 ቀን 2013 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ተዘግቶ ተወዳዳሪዎች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በዚሁ ቀን ከቀኑ 8፡30 በኩባንያው ቢሮ ቁጥር 09 ይከፈታል፡፡
 9.  ተጫራቾች በጨረታው ደንብና መመሪያ መሠረት ጨረታቸውን ማቅረብ አለባቸው፡፡ ከጨረታው ደንብና መመሪያ ውጭየሚቀርብ ማንኛውም ጨረታ ተቀባይነት የለውም፡፡
 10. ተወዳዳሪ ተጫራቾች ምን አይነት መሣሪያና ተሸከርካሪ እንደሚያከራዩና ብዛቱን ጭምር በግልጽ በፎርሙ ላይ መግለጽአለባቸው፡፡
 11. . ተወዳዳሪዎች የሚያከራዩበትን ዋጋ መሙላት የሚችሉት በዚሁ በኩባንያው በተዘጋጀው ፎርም ላይ ብቻ ይሆናል፡፡
 12. ተወዳዳሪዎች ሰነድ የገዙበትን ደረሰኝ ኮፒ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
 13. ተጫራቾች ለጨረታ የሚያቀርቧቸው ማሽነሪዎችና ተሸከርካሪዎች የሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ዋጋ ክፍል ሦስት ላይበተገለፀው መሠረት መሆን አለበት በተጨማሪ ለየትኛው ሎት እንደሚወዳደሩ በግልጽ መቀመጥ አለበት፡፡
 14. የሥራ ስምሪትን በተመለከተ፣ ተጫራቾቹ አሸናፊ የሆኑባቸውን መሣሪያዎች ከተገለፁላቸው በኋላ ለፕሮጀክቶች የማቅረቢያጊዜ ሲደርስ /05/ በአምስት ቀናት ውስጥ አሸናፊ የሆኑበትን መሣሪያዎች ወይም ተሽከርካሪዎች ውል እንዲፈርሙ ይደረጋል፡፡
 15. ተወዳዳሪው ድርጅቱ በጨረታ በተወዳደረበት ተሸከርካሪ እና ማሽነሪ ቁጥር ልክ መሣሪያዎችን ማቅረብ ይችላል፡፡
 16. ተወዳዳሪው ለሚያቀርባቸው ማሽነሪዎችና ተሽከርካሪዎች የባለቤትነት ማስረጃ ሊብሬ ኮፒ ማያያዝ እና ጨረታውበሚከፈትበት ጊዜ ለማመሳከሪያነትም ኦሪጅናል ሊብሬ ይዞ መቅረብ ይገባዋል፡፡
 17. አንድ ተወዳዳሪ ከራሱ መሣሪያና ተሽከርካሪ ውጪ የሚያቀርብ ከሆነ ሕጋዊ ውክልና እና የባለቤትነት ማስረጃ ሊብሬ ኮፒማያያዝ አለበት፡፡ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ለማመሳከሪያነትም ኦሪጅናል ሊብሬ ይዞ መቅረብ ይገባል፡፡
 18. ተወዳዳሪዎች በተቀመጠው ፎርም ላይ አስፈላጊውን መረጃ በመሙላት እና አባሪዎች ላይ በሙሉ ፈርመውበት የድርጅታቸውንማህተም ሊያደርጉ ይገባል፡፡
 19. ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ማሽነሪ/ተሸከርካሪ በፖሰታው ላይ ለምን አይነት ማሽነሪ/ተሸከርካሪ ብዛቱንም ጭምር ከላይበፖስታው ላይ በግልጽ ማሰቀመጥ እና ማህተም ማድረግ አለባቸው፡፡
 20. አመልካቾች የሚቀርቧቸውን የማሽነሪዎችና ተሽከርካሪዎች በሰንጠረዦቹ ላይ የተጠቀሱትን የመሥራት ወይም የመጫን አቅምያላቸው ሊሆን ይገባል፣ እንዲሁም ለመሣሪያዎቹና ለተሽከርካሪዎቹ የሚመድቧቸው ኦፕሬተሮች /ሾፌሮች/ ብቃት ያላቸውእና ስነ-ምግባር ያላቸው ሊሆኑይገባል፡፡
 21. አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች የሚጠሩት በአሸነፉበት ቅደም ተከተል ይሆናል፡፡
 22. . ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
 23. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058-320-25-48 ፋክስ ቁጥር 058-220-48-30 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የጢስ እሳት ውሃ ስራዎች ኃ/የተ/የግ/ማህበር