ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡ ጢእ/11/2020/ግጨ/7/03/2013
ጢስ እሳት ዉሃ ስራዎች ኃ/የተ/የግ/ማህበር Rolled sheet metal pipe (የላሜራና የመጠቅለያዉን ዋጋ አካቶ)፣ የመጠቅለያ የእጅ ዋጋ እና ሽት ሜታል 6ሚሜ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአቅራቢዎች ለመግዛት ይፈልጋል::
ተ.ቁ |
ሎት |
የዕቃዉ አይነት |
የጨረታ ማስከበሪያ |
ምርመራ |
1 |
ሎት 1 |
Rolled sheet metal pipe እና የመጠቅለያ የእጅ ዋ |
50,000.00 |
|
2 |
ሎት 2 |
ሽት ሜታል 6ሚሜ እና ሌሎች ዕቃዎች |
50,000.00 |
|
ስለዚህ ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራና በጨረታዉ መሳተፍ የሚፈልግ ተጫራች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟላ በጨረታዉ መሳተፍ ይችላል::ተጫራቾች የዘመኑን ግብር ከፍለው የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምሰክር ወረቀት፣የተጨማሪ እሴት ታክስ እና የቲን ሰርተፊኬት፣ማስረጃዎች ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል::
- ጨረታው ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ማለትም ከህዳር 7/03/2013 እስከ ህዳር 21/3/2013ዓ.ም ለ15 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ የሚቆይ ሲሆን በ15ኛው ቀን ህዳር 21/3/2013 ዓ.ም ከቀኑ 10፡00 ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከቀኑ 10፡30 ባህርዳር ከተማ አባይ ማዶ ቴዲ የአሸከርካሪዎች ማሰልጠኛ ጎን በሚገኘው ዋናዉ መ/ቤት ተጫራቾች እና ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል:: የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት ተዘግቶ ይከፈታል::
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በኩባንያችን አባይ ማዶ ቴዲ የአሸከርካሪዎች ማሰልጠኛ ጎን በሚገኘው ዋናዉ መ/ቤት ቢሮ ቁጥር 002 የማይመለስ 100.00 ብር (አንድ መቶ ብር) በመክፈል የመጫረጫ ሰነዱን መዉሰድ ይችላሉ::
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት በሎት ከላይ በተቀመጠዉ በሰንጠረዥ መሰረት ተቀባይነት ባላቸው የአፈጻጸም ዋስትናዎች (ቢድ ቦንድ) በባንክ በተረጋገጠ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው::
- ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያቸዉን እና የጨረታ ማስከበሪያዉን በተለያየ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል:: ተጫራች ድርጅቶች ለሚያቀርቡት ዋጋ ለእያንዳንዱን ዕቃ ነጠላ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ በትክክል ሞልተው በግልጽ ማስቀመጥ አለባቸው::
- ይህ ጨረታ በኩባንያችን የግዥ መመሪያ Miyazya /2009/ መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል::
- የጨረታዉ አሸናፊ አሸናፊነቱ በጽሁፍ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ5 የስራ ቀናት ዉስጥ የጠቅላላ ዋጋዉን 10 በመቶ የዉል ማስከበሪያ ያለቅድመ ሁኔታ ለገዥ የሚከፈል በማሰራት ዉል የመያዝ ግዴታ ይኖርበታል::
- የማቅረቢያ ጊዜ ከ15 እስከ 25 ቀናት መሆን አለበት:: የአቅራቢዎች ዋጋ ቢያንስ ለ90 ቀናት ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ፀንቶ መቆየት አለበት::
- ኩባንያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ በዚህ ጨረታ አይገደድም ወይም ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥራችን 058-220-48-26 /0583202548/ በፋክስ ቁጥራችን 0582204830 መጠየቅ ይችላሉ::
የጢስ እሳት ዉሃ ስራዎች ኃ/የተ/የግ/ማህበር