የግንባታ ሥራ ጨረታ ማስታወቂያ
ጋለማ የገበሬዎች ሥራዩኒየን በኦሮሚያ ክልል ኦርሲ ዞን በቆጂ ከተማ የሚገኘው ዩኒየናችን በሳጉሬ ከተማ የመካናይዜሽን እገልግሎት ማእከል ( Mechanization Service Center) የሚውል ህንጻ ብቁ የሆኑ ተጫራቾችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ ፡
ተቁ |
የፕሮጀከቱ ሥራ |
ዞን |
ከተማ |
ስፋት ርዝመት
|
የጨረታ ማስከበሪያ |
የኮንስትራክሽን ጊዜ |
የሚፈለገው ደረጃ |
1 |
የመካናይዜሽን አገልግሎት ማእከል (Mechanization Service Center)
|
አርሲ |
ሳጉሬ |
በዲዛይኑ መሠረት
|
የዋጋ ግምቱን 2%
|
90 ቀናት |
ደረጃ 5 BC/ GC እና ከዚያ በላይ |
- ተጫራቾች በሰንጠረዡ የተቀመጠውን ደረጃ የሚያሟሉ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የንግድ ፍቃዳቸውን ያሳደሱ ፍቃዳቸውን ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን ማቅረብ የሚችሉና የተፅታ (VAT) ተመዝጋቢ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቶች በቂ የስራ ልምድ ያላቸው ለዚሁም ተያያዥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ከስራና ከተማ ልማት ወይም ከኮንስትራክሽንና ቤቶች ልማት ሚኒስቴር ወይም ከኦሮሚያ ስራና ከተማ ልማት ወይም ከኦሮሚያ ከሚመለከታቸው ፍቃድ ሰጪ አካል የተጠቀሰው የግንባታ ፍቃድ ያላቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር ሰነድ (የስራ መጠንና አሰራር እንዲሁም ዲዛይን) ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 ተከታታይ የስራ ቀናት ጋለማ የገ |ሕ| ሥራ ዩኒየን ፅ/ቤት ዘወትር በሥራ ሰዓት በመቅረብ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ::
- ተጫራቾች የሰነድ መግዣ 400.00 (ኦራት መቶ) ብር በሂሳብ ቁጥራችን ጋለማ የገበሬዎች ኅብረት ስራ ዩኒየን ኢትዮጵያ ንግድ ባንከ በቆጂ ቅርንጫፍ የሂሳብ ቁጥር 1000041394618 ገቢ በማድረግ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይኖርባችኋል፡፡
- ተጫራቾች ጠቅላላ የስራ ዋጋውን በቁጥርና በፊደል ዋጋ ማጠቃለያው ላይ መፃፍ አለባቸው:: በቁጥርና በፊደል የተገለፀው የዋጋ መጠን መካከል አለመጣጣም ካለ በፊደል የተገለፀው ተቀባይነት ይኖረዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ በአንድ ኦርጅናልና ሁለት ፎቶ ኮፒ በማዘጋጀት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ እንዲሁም ሁለቱንም ሰነድ በአንድ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማዘጋጀት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለ21 ተከታታይ የስራ ቀናት እንዲሁም በ 25ኛው ቀን እስከ 4፡30 ሰአት በጋለማ ዩኒየን ፅ/ቤት በቆጂ ዘወትር በሥራ ሰዓት በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የሚቻል ሲሆን፤ ጨረታውም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ21ኛው ቀን ይህም ከጠዋቱ በ4:30 ሰዓት ታሽጎ (በዚያው ዕለት ከጠዋቱ 4፡45 ሰዓት በጋለማ ዩኒየን ፅ/ቤት ይከፈታል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች በጋለማ የገ/ህ/ሥራ ዩኒየን ስም የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ CPO ወይም የባንክ ዋስትና (Bank Guarantee) የዋጋ ግምቱን 2% ከዋጋ ማቅረቢያ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ በጨረታው የተሸነፈ ተጫራች CPO ወይም የባንክ ዋስትና(Bank Guarantee) ወዲያው ይመለስለታል፡፡
- ጨረታውን ያሸነፈ ድርጅት የአሸናፊነት ደብዳቤ ከደረሰው በኋላ ከዩኒየኑ ጋር የውል ስምምነት ይፈርማል፡፡
- አሸናፊው ተጫራች ቅድመ ክፍያ 20% መውሰድ ከፈለጉ የሚወስደውን ብር መጠን የሚስተካከል ዋስትና ማቅረብ አለበት፡፡
- አጠቃላይ የግንባታ ሥራው ወጪ የሚሸፈነው በአሸናፊ ተጫራች ሆኖ ዩኒየኑ ክፍያ የሚፈፅመው ስራው በመሐንዲስ/በባለሙያ እየተረጋገጠ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ሌላ ስራ ላይ ከሆኑ በዚህ ጨረታ ለመሳተፍ ቢያንስ 70 ፐርሰንት ማጠናቀቅ ይኖርባቸዋል፡፡
- ዩኒየኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 022-332-0006/022 332-01-84
ጋለማ የገበሬዎች ኅብረት ሥራ ዩኒየን በቆጂ