በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የገቢዎች
ሚኒስቴር በታክስ ዕዳ ያያዛቸውን ንብረቶች ለመሽጥ
የወጣ የግልጽ ጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ ቁ-3/2013
የሚኒስቴር መ/ቤቱ ግብር ከፋዮች የሚጠበቅባቸውን የታክስ ዕዳ በታክስ ህጉ በተፈቀደው የጊዜ ገደብ ባለመክፈላቸው ምክንያት በታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀፅ 41 በተሠጠው ስልጣን መሠረት ዋናው መ/ቤት ከፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በተከራያቸው ጨው በረንዳ አካባቢ በሚገኘው የተሽከርካሪዎች መጋዘንና ሳሪስ አደይ አበባ አካባቢ በሚገኘው የንብረቶች መጋዘን ከፎርማሲስ የትምህርትና የስልጠና አማ፣ የተያዙ የተለያዩ የቢሮ መገልገያ ዕቃዎችን ፣ ከጌታነህ ትሬዲንግ እና የሸበል ኃ/የተ/የግ/ማህበር የተያዙ የተለያዩ ንብረቶች፣ ከካለወርክ ኢትዮጵያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር የተያዙ ከአልሙኒየም የተሰሩ የተለያየ መጠን ያላቸው የተጠናቀቁና ያልተጠናቀቁ
- የብረት ድስትና ማንቆርቆሪያ ምርቶች፣ እንዲሁም
- የቫይቴክስ ትሬዲንግ፣ የአዲስ ተፈጥሮ ሀብት ልማት፤ የዩናትድ በራዘር እና የባዘቶ ኃ/የተየግ/ማህበር ንብረት የሆኑ ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል::
በመሆኑም፡-
- በግልጽ ጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ እና የታደሰ ንግድ ፈቃድ፤ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዞ በኢንቨሎፕ በማሸግ ለግልጽ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል።
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ የግልጽ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ እና ቅዳሜ ጠዋት ከ2፡00-6፡00 ሰዓት ህንፃ “መ” 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 301 ከግዥና ፋይናንስ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ህንፃ “ሀ” 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 202 በታክስ ዕዳ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ መውሰድ ይኖርበታል፡፡
- በግልጽ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ተሽከርካሪዎች /ንብረቶች/ የሰጡትን ዋጋ 1/10ኛውን ብቻ ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (CPO) በገቢዎች ሚኒስቴር ስም (Ministry of Revenue) በባንክ አሰርተው ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በሚከተለው የጨረታ ቀናት (ስኬጁል) መሰረት ሰነድ ገዝተው መጫረት ይችላሉ፡፡
ተ/ቁ |
የመ/ቤቱ ስም |
ለጨረታ የቀረበው የንብረት ዓይነት |
የንብረቶቹ መመልከቻ ቀን |
የጨረታው የመዝጊያ እና የመክፈቻ ቀንና ሰዓት |
1 |
ገቢዎች ሚኒስቴር |
የተለያየ ሞዴል ያላቸው ተሽከርካሪዎች፤ የተጠናቀቁና ያልተጠናቀቁ የብረድስት ምርቶች፣ የቤትና የቢሮ መገልገያ ዕቃዎች
|
ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ቀናት
|
ማስታወቂያው በጋዜጣ ወጥቶ 15 ቀን ከተጠናቀቀ በኋላ ቀጥሎ ባለው 16ኛ ቀን 3፡45 ተዘግቶ በዚያኑ ቀን በ4፡00 ሰዓት ይከፈታል። |
5. የጨረታ መክፈቻ ቦታ፡– መገናኛ በሚገኘው በሚኒስቴር መ/ቤቱ ህንፃ “መ” 6ኛ ፎቅ ተጫራቶች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ወይም በታዛቢዎች ፊት ይከፈታል።
6.የግልጽ ጨረታው መክፈቻና መዝጊያ 16ኛው ቀን የመ/ቤቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ ቀን የግልጽ ጨረታው መክፈቻና መዝጊያ ቀን ይሆናል፡፡
7. ለጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ ዋስትና ያስያዙት (CPO) ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር እንደ አስፈላጊነቱ የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ የግልጽ ጨረታ ኮሚቴው መረጃውን አጣርቶ እንደጨረሰ በ5 የስራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡
8. የተሽከርካሪ ጨረታ ለሚያሸንፉ ተጫራቾች ከስመ–ንብረት ዝውውር ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ወጪዎች (የቦሎና ሌሎች ተጓዳኝ ወጪዎች ሻጭን አይመለከትም፡፡
9. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን በደብዳቤ ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ መ/ቤቱ በሚሠጠው አድራሻ ገቢ በማድረግ ያሸነፋበትን ንብረት ሀብት መረከብ ይኖርባቸዋል፡፡
10. ከላይ በተ/ቁ 9 በተገለጹት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ በማድረግ ንብረታቸውን ያልተረከቡ ተጫራቾች የግልጽ ጨረታው ተሠርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት የዋስትና ገንዘብ ለሚኒስቴር መ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ንብረቱ እንዳልተሸጠ ተቆጥሮ በቀጣይ በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል፡፡
11. ሚኒስቴር መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ የግልጽ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡– 011 662-98-37 ደውለው መጠየቅ ወይም የተቋሙን ዌብሳይት WWW.MORGov.et መመልከት ይቻላል፡፡
ገቢዎች ሚኒስቴር