የጨረታ ማስታወቂያ
ዶንኪ ሳንክችዋሪ ኢትዮጵያ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
ስለዚህ በጨረታው መሳተፍ ስሚፈልጉ ማንኛውም ተጫራቾች
- የተሽከርካሪዎች ዓይነትና ዝርዝር በጨረታው ሰነድ ላይ የሚገኝ ሲሆን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ጊዜ አንስቶ እስከ ግንቦት 28/2012 ዓ/ም ድረስ ቦሌ መንገድ ሳይ ህንፃ 4ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የድርጅቱ አስተዳደር ቢሮ በመቅረብ የጨረታውን ሰነድ መውሰድ የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
- ተሽከርካሪዎቹን በአካል ማየት ለሚፈልጉ ተጫራቾች በድርጅቱ አስተዳደር ቢሮ በመቅረብ ድርጅቱ በሚያዘጋጀው አስጎብኚ ማየት የሚችሉ መሆነን ስንገልፅ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነዱን የወሰዱ ተጫራቾች ብቻ በተቀመጠው ፕሮግራም መሠረት ግንቦት 21/2012፣ ግንቦት 24/2012 እና ግንቦት 27/2012 ዓ/ም ከጥዋቱ 4፡00 ሰዓት እስከ 10፡00 ሰዓት ማየት ይችላሉ።
- ተጫራቾች እያንዳንዱን ተሽከርካሪ የሚገዙበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ እስከ ጨረታው መዝጊያ ቀን ድረስ በድርጅቱ አስተዳደር ቢሮ በአካል ወይም በህጋዊ ወኪሎቻቸው በመቅረብ እስከ ቀኑ አስር ሰዓት ማስገባት ይችላሉ።
- የሚጫረቱበትን ተሽከርካሪ መነሻ ዋጋ 5% በባንክ ክፍያ መያዣ (ሲፒኦ) የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የጨረታ ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስ፣ የስም ዝውውር እና ቀረጥ ላልተከፈለባቸው ተሽከርካሪዎች ቀረጡን እንዲሁም ተያያዥ የመንግሥት ክፍያዎችን የሚከፍሉ መሆኑን እንገልፃለን።
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ያልያስያዘ ተጫራች ሰነዱ ተቀባይነት አይኖረውም።
- ጨረታው ግንቦት 28/2012 ዓ.ም ተዘግቶ ግንቦት 29/2012 ዓ.ም የሚከፈት ሲሆን የአሸናፊዎቹም ስም ዝርዝር በድርጅቱ የማስታወቂያ ቦርድ ላይ የሚለጠፍ ይሆናል። በጨረታው ያላሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ሲፒኦ ሰኞ ሰኔ 1/2012 ዓ.ም ከድርጅቱ አስተዳደር ቢሮ ቀርበው መውሰድ ይችላሉ።
- ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን መሉ በመሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ዘ ዶንኪ ሳንክችዋሪ ኢትዮጵያ
ቦሌ መንገድ ላይ ህንፃ 4ኛ ፎቅ
ስልክ 0116 185708
ፖ.ሳ.ቁ. 1055/1250