ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የድ/ቴ/ሙ/ማ/ኮሌጅ የግዥ/ፋይ/ንብ/አስ/ ቡድን ለኮሌጃችን አገልግሎት የሚውል በ2ዐ13 ዓ/ም በጀት አመት ለሚገዙ ዕቃዎች ማለትም
- ሎት 1 የስቴሽነሪ ዕቃዎች
- ሎት 2 ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች
- ሎት 3 የውጭ ስሪት ወንበር
- ሎት 4 የቤትና የቢሮ ዕቃዎች
- ሎት 5 የጽዳት ዕቃዎች
- ሎት 6 የተዘጋጁ የደንብ ልብሶች
- ሎት 7 ጫማዎች
- ሎት 8 ብትን ጨርቃ ጨርቅ
- ሎት 9 የጎማ በርሜሎች
- ሎት 1ዐ የህንፃ መሣሪያዎች
- ሎት 11 ህትመት
- ሎት 12 የእንስሳት መድሀኒት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም መጫረት የምትፈልጉ ሁሉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባችኋል፡፡
- በአዲሱ አዋጅ መሰረት የታደሰ ንግድ ስራ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው
- የግዥ መጠን ብር 200 ሽህ ብርና ከዚህ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር ከ1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃ ኦርጅናልና ፎቶ ኮፒ ለየብቻው በማሸግና በእያንዳንዱ ፖስታ ላይ የአሰሪው መስሪያ ቤትና የተጫራቹን ሙሉ ስምና አድራሻ ፊርማና ማህተም በማስቀመጥ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸውል፣
- አሸናፊ ተጫራች ማሸነፍ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ከ5 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የጨረታ አሸናፊው የውል ማስከበሪያ ጠቅላላ ዋጋን 1ዐ በመቶ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመ/ሂ1 ማስያዝ አለባቸው፣
- የሚገዙ የዕቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ /እስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፣
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 50 ብር በመክፈል ቢ/ቁ 02 ማግኘት ይችላሉ፣
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩትበት የዕቃውን ጠ/ዋጋ 2 በመቶ በሁነታ ላይ ያልተመሰረተ በባንክ የተረጋገጠ የባንክ ዋስትና የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ወይም በጥሬ ገንዘብ በመሂ1 ማስያዝ አለባቸው
- ተጫራቾች የጨረታ ሃሳባቸውን ዋናውንና ቅጁን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በድጎ ዕዮን ቴ/ሙ/ማ/ኮሌጅ የግ/ፍ/ን/አስ/ቡድን ቢ/ቁ 05 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ከ12/04/2013 ዓ/ም እስከ 26/03/2013 ዓ/ም እስከ 11፡30 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም የግዥ/ፋይ/ንብ/አስ/ ቡድን ቢ/ቁ 05 በ16ኛው ቀን በ27/03/2013 ዓ/ም 3፡00 ታሽጎ በዚህ ቀን 3፡30 ይከፈታል፡፡
- ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ኮሌጁ 2ዐ በመቶ የመጨመር ወይም የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ከላይ በሎት ከተዘረዘሩ ዕቃዎች ውስጥ ኮሌጁ የዕቃዎችን ናሙና በሚፈልግበት ጊዜ እንዲያቀርቡ የሚጠይቅ መሆኑን እደንገልፃለን፡፡
- በሌላ በኩል አሸናፊው ድርጅት ዕቃዎችን በሙሉ በኮሌጁ ውስጥ ሊያቀርቡና በጥራት ኮሚቴው ተረጋግጦ ገቢ ይሆናል፡፡
- ኮሌጁ ጨረታው በሚከፈትበት ቀን የበዓላት ቀን ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ቀን ይከፈታል፡፡
- በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢ/ቁ ዐ5 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0582540497/0582540331 በመደውል ማግኘት ይችላሉ፡፡
ድጎ ጽዮን ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ