ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
ደብረታቦር ከተማ አስ/ኢ/ል/ከተማ አገልግሎት ጽ/ቤት በ2012 ዓ.ም የበጀት ዓመት ከሚያሠራቸው የመሰረተ ልማት ግንባታዎች ውስጥ፡
- ቀበሌ 01 አስተዳደር ከልዑል አለማየሁ አባ ጓዴ ጀበል 140 ሜትር ጠጠር መንገድ፣
- ከታቦር ት/ቤት በሆማው ልጅቱ ማሪያም ኮብል እስቶን መንገድ ድረስ 1430 ሜትር ጠጠር መንገድ በGC እና BC በደረጃ 7 እና በላይ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡
በዚህ መሠረት የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟላ ተጫራች መወዳደር የሚችል መሆኑን ይጋብዛል፡:
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ /ቲን/ ቁጥር ያላቸው፡፡
- የቫት ተመዝጋቢ መሆንዎን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ አለብዎት፡፡
- ተጫራቾች ከተ/ቁ 1-3 የተዘረዘሩትን መረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የግንባታ ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነድ ማግኘት የሚቻል ሲሆን የአንድ ሰነድ ዋጋ ብር 300.00 /ሦስት መቶ ብር/ ብቻ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- ስርዝ ድልዝ የሚያጋጥም ከሆነ ፓራፍ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ካልተደረገ ከውድድሩ ውጪ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ የመንገድ ግንባታ የሚወዳደሩበትን የእቃውን ጠ/ዋጋ ብር 50,000.00 /ሃምሣ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ወይም ከቴ/ሙ/ኢ/ጽ/ቤት ድጋፍ ማስያዝ ይችላሉ፡፡
- የግል ኮንትራክተሮች ያሸነፉበትን ዋጋ ቢያንስ 10 በመቶ የመንግሥት ልማት ድርጅት ቢያንስ 15 በመቶ ለተደራጁ ኢንተርፕራይዞች መስጠት አለባቸው፡፡
- የጨረታ ሣጥኑ ቤቶችና መሰረተ ልማት ቢሮ ይገኛል፡፡ ጨረታው የሚከፈተው ቤቶችና መሰረተ ልማት ቢሮ ነው፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ሲያገኝ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ጨረታው ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ላሉት 21 ተከታታይ ቀናት ይቆያል፡፡ ውድድሩ በእያንዳንዱ ሎት ድምር መሆኑን እንገልፃለን፡፡ ሁሉንም ዝርዝር ያልሞላ ከውድድሩ ውጪ ይሆናል፡፡
- ጨረታው በ22ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ታሽጐ በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ነገር ግን የመጨረሻው ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡
- ለማንኛውም ተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 058 441 0203/058 141 00 91 እና 058 44 0058 መጠየቅ ይችላሉ፡፡
ደብረታቦር ከተማ አስ/ኢ/ል/
ከተማ አገልግሎት ጽ/ቤት