የተለያዩ ቁሳቁሶችን ለመሸጥ ለ3ኛ ጊዜ
የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
- በመፍረስ ላይ ያለው ደልቢ ኮል ማይኒንግ አ.ማ. በጅማ ዞን ዴዶ ወረዳ ደልቢ ቀበሌ አስተዳደር ውስጥ የሚገኘውን እና ሲጠቀምባቸው የነበሩ የተለያዩ የማይኒንግ፣ የቢሮ፣ የመኪና መለዋወጫዎችና የመኪና ሚዛን(ዌይት ቢርጅ) ጨምሮ በግልፅ ጨረታ ለመሸጥ ስለሚፈልግ መግዛት የሚፈልግ ግለሰብ (ኩባንያ) የቁሳቁሶቹን ዝርዝር የያዘ ሰነድ ብር 100 በመክፈል በጅማ ከተማ አቡነ እስጢፋኖስ ህንጻ 6ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 515 ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ እስከ ኅዳር 20/2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:00-10:00 ሠዓት ባለው ጊዜ በመግዛት እና ለሚያቀርበው አጠቃላይ የመወዳደሪያ ዋጋ 10% በባንክ CPO በማስያዝ ከኅዳር 21-ኅዳር 24 ቀን 2013 ከቀኑ 6፡00 ድረስ ብቻ ለዚህ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስገባት ይችላል።
- ጨረታው በ24/3/2013 ዓ.ም ከቀኑ 6፡00 ተዘግቶ በዕለቱ በ24/3/2013 ዓ.ም ከቀኑ በ8፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪል ባለበት ይከፈታል።
- የጨረታ አሸናፊዎች ያሸነፉበትን ዕቃ በ5 የሥራ ቀናት ውስጥ ዋጋውን ሙሉ በሙሉ በመክፈል መረከብ ይኖርባቸዋል። ይህን የማይፈፅሙ ተጫራቾች ያስያዙት የCPO ዋስትና ለማኅበሩ ገቢ ይሆናል።
- ንብረት አጣሪ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0911-7562-75/047-111-7060
ሰብለ አሰፋ እና ጓዶቿ የሕግ አማካሪ /ንብረት አጣሪ/