የሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ
የምዕራብ ጎጃም ዞን የፍኖተ ሰላም ከተማ ልማት ቤቶች ኮንስትራክሽን አገልግሎት ጽ/ቤት መሬት ባንክ ቡድን የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ 721/2004 አንቀጽ 8 ንዑስ አንቀጽ 1 በፊደል ተራ ከሀ እስከ ሠ በተዘረዘረው መሰረት የመኖሪያ እና የድርጅት ኤገልግሎቶች የተዘጋጀ ቦታን በግልጽ ጨረታ ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም መጫረት የሚፈልግ ማንኛውም ሰው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ከ08/10/2012 ዓ/ም ጀምሮ የቦታውን ዝርዝር መረጃ እና የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ለመኖሪያ 300 ብር ለድርጅት 400 በመክፈል በአድራሻ ቢሮ ቁጥር 76 በስራ ሰዓት መግዛት የሚቻል መሆኑን እናስታውቃለን፡፡
- የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ጊዜ ከ08/10/2012 ዓ/ም ጀምሮ እስከ 19/10/2012 ዓ/ም ከቀኑ 11፡00 ብቻ ይሆናል፡፡
- ጨረታው የሚዘጋው በ19/10/2012 ዓ/ም በ11፡00 ይሆናል፡፡
- ቦታውን መጎብኘት ለሚፈልግ ተጫራች በተቋሙ ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ በሚገለፀው መርሃ ግብር መሰረት የምናስጎበኝ ይሆናል፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው በ22/10/2012 ዓ/ም ከጠዋቱ በ3፡00 በቀበሌ 01 አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይሆናል፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ በፍ/ሰላም ከ/አስ/ቤ/ኮ/አገ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 76 ማግኘትይቻላል፡፡
- መስሪያ ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 058 7750813 ወይም 058 7751775 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
የፍኖተ ሰላም ከተማ ልማት ቤቶች ኮንስትራክሽን አገልግሎት ጽ/ቤት