የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር
ፌ/ፖ/ት/003/2013 ዓ.ም
የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ጤና አገልግሎት ምክትል ዘርፍ 2013 ዓ.ም የበጀት ዓመት በ2013 በጀት ዓመት ለሰርቪስ አገልግሎት የሚውል የመኪና ኪራይ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት የሚፈልግ ስለሆነ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ከስራው ጋር የተገናኘ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የሀገር ውስጥ ገቢ የድጋፍ ደብዳቤ 6 ወር ያላለፈበት፣ በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚ/ር በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡበትን ምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሠርተፊኬት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ቲን ነምበር፣ የመኪና ሊብሬ ኢንሹራንሽ እና ሰፕላየር ሊስት /supplier , list/ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን ዝርዝር መግለጫ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 150.00 /አንድ መቶ አምሳ ብር/ በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 /አስራ አምስት ቀናት /ከጠዋቱ 2:30 ሰዓት እስከ 9:30 ሰዓት ድረስ የፌዴራል ፖሊስ ጤና አገልግሎት ም/ ዘርፍ ፋይናንስ ዲቪዥን ሁለተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 23 ቀርበው በመግዛት የመጫረቻ ሰነዳቸውን በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ በማድረግ ቢሮ ቁጥር 32 እስከ 5ኛው ቀን ድረስ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የሚችሉ ሲሆን ጨረታው በ15ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን 15ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተባለው ጊዜና ቦታ የሚከፈት ይሆናል መ/ቤታችን ስለጨረታሠነዱ መጥፋት ወይም መዘግየት ኃላፊነት አይወስድም፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ (BD BOND) ብር 10,000.00/አስር ሺህ ብር/ ከታወቀ ባንክ የሚሰጥ በሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብና በባክ ጋራንት ማቅረብ ይችላሉ። መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡ አድራሻ ልደታ ከተማ ባልቻ ሆስፒታል ጎን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ጤና አገልግሎት ም/ ዘርፍ ለበለጠ መረጃ 011-5-30-20-19
የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ጤና አገልግሎት ዘርፍ