በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት በ2013 በጀት ዓመት የሚውል የህትመት አገልግሎት ከህጋዊ አቅራቢዎች በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚሁም መሰረት ከታች የቀረበውን መስፈርት የሚያሟሉ አቅራቢዎችን ይጋብዛል፡፡
- ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ፣ በዘርፉ የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ከገቢዎች መ/ቤት የተሰጠ ክሊራንስ ወይንም የድጋፍ ደብዳቤ እና በግዥ ኤጀንሲ ድህረ ገፅ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ሙሉ ሰነድ ሶፍት ኮፒ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ስዓት የማይመለስ ብር 50.00/ ሀምሳ ብር/ በመክፈል ቦሌ መንገድ ከፍላሚንጎ ወደ ኤግዚቢሽን ማእከል ወደሚወስደው መንገድ 300 ሜትር ገባ ብሎ የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት ቢሮ ቁጥር 202 ጽ/ቤት መግዛት ይችላሉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም፡፡
- ተጫራቾች መጫረቻ ሰነዳቸውን በሁለት ኤንቨሎፕ የፋይናንሻል እና የቴክኒክ ሰነዳቸውን ለየብቻ በማዘጋጀት ኦርጅናል እና ኮፒውን ለየብቻ በማሸግ በአጠቃላይ በ4 ፖስታዎች በማድረግ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስራ አምስት ተከታታይ ቀናት እስከ ጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ የሚወዳደሩበትን የጨረታ ሰነድ እና በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣ ጀምሮ በተከታታይ በሚቆጠር በ15ተኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ ወዲያውኑ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾቹ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሮ ቁጥር 203 ይከፈታል፡፡
- ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የሚቀርቡ የመጫረቻ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
- የጨረታ መክፈቻ ቀኑ 15ኛው ቀን የስራ ቀን ላይ ያልዋለ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ /ቢድ ቦንድ/ ከሚያቀርቡት ከጠቅላላ ዋጋ ላይ 2% እና ከዚያ በላይ በማስላት በባንክ በተረጋገጠ /ሲፒኦ/ በማስያዝ ደረሰኙን በቴክኒክ ሰነድ ውስጥ አብረው በማካተት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሂደቱን ለማዛባት የሞከረ እንደሆነ ከጨረታው የሚሰረዝ እና ለወደፊቱም በመንግስት ግዥ ጨረታ እንዳይሳተፉ የሚደረግ ሲሆን ያስያዘውም የጨረታ ማስከበሪያ ለመንግስት ገቢ ይደረጋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታው አሸናፊነት ከተገለፀ በኋላ በ5 ቀናት ውስጥ ቀርበው ውለታ ካልፈፀሙ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይሆናል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ–ቦሌ መንገድ ከፍላሚንጎ ወደ ኤግዚቢሽን ማእከል ወደሚወስደው መንገድ 300 ሜትር ገባ ብሎ
ስልክ ቁጥር፡– 0118333730 ፖሳቁ 457
የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት