በድጋሚ በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በዋግኸምራ አስተዳደር ዞን የፃግብጂ ወረዳ ገ/ኢ/ት ጽቤት ለሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል
- የህንፃ መሣሪያ፣
- አጠና፣
- የመስታወት ሥራ፣
- ኤሌክትሮኒክስ ዕቃ ፣
- የህትመት ውጤቶች፣
- የፈርኒቸር ዕቃዎችን በ2013 ዓ.ም በጀት ግዥ መግዛት ይፈልጋል::
በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ይጋብዛል::
- በየዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ( TIN)
- የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ 1% ወይም ሲፒኦ በጥሬ ገንዘብ መ/ቤታችን ገ/ያዥ ገቢ በማድረግና ገቢ ያደረጉበትን ደረሰኝ ኮፒ በማድረግ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- የዕቃዎቹን አይነት ዝርዝር መግለጫ/ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር ብቻ/ ለእያንዳንዱ በመክፈል (ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ከ 27/1/2013 ዓ.ም እስከ 11/2/2013 ዓ.ም ለተከታታይ 15 ቀናት ፃ/ወ/ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ቢሮ በመምጣት መወሰድ ይችላሉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጆች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ፃ/ወ/ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል::
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኘበት ቀን በ12/2/2013 ዓ.ም 3:30 ሰዓት ታሽጎ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ የሚከፈት መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ጨረታው ስርዝ ድልዝ ወይም የማይነበብ ሰነድ ተቀባይነት የለውም::
- ተጫራቾች በጨረታው ማሸነፋቸው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የውል ማስከበያ አስይዘው ውል ካልፈፀሙ የጨረታ ማስከበሪያ ውርስ ይሆናል::
- በጨረታው ላይ ቅሬታ ያላቸው ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ እና አሸናፊው ከተለየ በ5 የስራ ቀናት ውስጥ ቅሬታቸውን ለሚመለከተው አካል ማቅረብ ይችላሉ::
- ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም::
- የጨረታ አሸናፊው የሚለየው በሎት ወይም በነጠላ ይሆናል::
- ጨረታውን ለመሳተፍ የሚፈልጉ ሁሉ የጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በወረዳው ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 7 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ 033 811 95 80 በመደወል ማግኘት ይችላሉ::
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በዋግ ኸምራ ዞን
የፃግብጂ ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት