ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በዋግ ኸምራ ብሔረሰብ አስተዳደር የፃግብጂ ወረዳ የገ/ኢ/ትብብር ጽ/ቤት የፃ/ወ/ገጠር መንገድና ትራንስፖርት ጽ/ቤት በወረዳው ውስጥ ያለው መንገድ ለሚሰራው የሰርቪስ አገልግሎት የሚሰጥ ሲንግል ካፕ መኪና /LAND CRUIZER ተከራይቶ ማሰራት ይፈልጋል::
ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ይጋብዛል ::
- በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው::
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ::
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር(TIN) ነበር ያላቸው::
- የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ::
- የስሪት ዘመኑ ከ2015 G.C ጀምሮ::
- የነዳጅ ፍጆታ ወይም ኖርማላይዜሽን ተሰርቶ መያያዝ አለበት::
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-5 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ ቫትን ጨምሮ 1% በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ከመ/ቤታችን ገ/ያዥ ገቢ በማድረግና ገቢ ያደረጉበትን ደረሰኝ ኮፒ በማድረግ ማያያዝ አለባቸው::
- የሥራው አይነት ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን / ከጨረታ ሰነድ ማግኘት ይችላሉ::
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ከ27/1/2013 ዓ.ም እስከ 11/2/2013 ዓ.ም ለተከታታይ 15 ቀን 11፡30 ሰዓት ድረስ ጨረታው በአየር ላይ የሚቆይ መሆኑን እየገለፅን ሰነድ መግዛት የሚቻለው ግን በስራ ሰዓት ሲሆን በ16ኛ ቀን በ12/2/2013 ዓ.ም 3፡30 ሰዓት ድረስ የገዙትን ሰነድ አስገብተው 4፡00 ሰዓት ላይ ይከፈታል:: ጨረታው የሚከፈተው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሲሆን በሰዓቱ ካልተገኙ ጽ/ቤቱ በሌሉበት የመክፈት መብቱ የተጠበቀ ነው::
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን ለአንድ ወይም አንድ ወጥ ሲሆኑ ሁለት ቅጆች ማለትም ዋናና ቅጅ በሎት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ፃ/ወ/ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ግዥ ቡድን መሪ ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ስዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በሚከፈትበት ቀን ካላንደር ወይም ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል::
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው:: ጨረታው ስርዝ ድልዝ ወይም የማይነበብ ሰነድ ተቀባይነት የለውም::
- በዚህ የጨረታ ማስታወቂያ ያልተካተቱ ህግና ደንቦች ለግዥ መመሪያ ቁጥር 1/2003 ተግባራዊ ይደረጋል፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ሁሉ የጨረታውን ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በወረዳው ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ግዥ ቡድን መሪ ቢሮ ድረስ በአካል መገኘት ይችላሉ፡፡
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር
የፃግብጂ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት