የጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ መለያ ቁጥር 001/2013
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በጉለሌ ክ/ከተማ የወረዳ 3 ት/ጽ/ቤት የፀሐይ ጮራ የመጀ/ደ/ት/ቤት ለ2013 ዓም በመበደኛ በጀት እና በድጐማ በጀት ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውሉ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
- ሎት1 ፡– የደንብ ልብስ እና የደንብ ልብስ ማሰፊያ፣
- ሎት2፡– አላቂ የቢሮ እቃዎች፣
- ሎት3፡– የትምህርት እቃዎች ፣
- ሎት 4 ፡– አላቂ የፅዳት እቃዎች፣
- ሎት5 ፡– የጥገና እቃዎች ፣
- ሎት 6፡– አላቂ የሕክምና እቃዎች
- ሎት7፡– ህትመት
ስለሆነም በጨረታ መሳተፍ የሚፈልጉ የንግድ ድርጅት
- በዘርፉ ህጋዊና የታደሰ ኦርጅናል የንግድ ፈቃድ ያላቸው በግዥ ኤጀንሲ ፋይናንስ ቢሮ በእቃአገልግሎት አቅራቢያዎች ሊስት /ዝርዝር/ የተመዘገቡና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት ስለመመዝገባቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ስለጨረታው የሚገልጽ የጨረታ ሰነድ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት የማይመለስ ብር 100.000 /አንድ መቶ ብር/በመከፈል ሰነዱን ከት/ቤቱ ፋ/ግ/ን/አስ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 20 መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በየሎት ከተቀመጠው የመግዣ ዋጋ ማለትም ሎት 1 ፡– 6,000.00፣ ሎት 2፡3,000.00፣ ሎት3፡– 2377.60 ፣ሎት 4፡7,000.00 ሎት5 ፡– 2,000.00 ሎት 6፡-60.00- ሎት7፡– 400.00 በባንክ የተመሰከረለት የክፍያ ማዘዣ /cpo/ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ከመጫረቻ ዋጋው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል የመጫረቻ ዋጋው ቫትን ማካተት ይኖርበታል ቫትን ያላካተተ የመጫረቻ ዋጋ ለውድድር አይቀርብም፡፡
- ናሙና ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች ጨረታውን ከመዘጋቱ በፊት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ናሙና ያላቀረቡ ተጫራቶችከጨረታው ይሰረዛሉ። ናሙና የማይቀርብላቸው እቃዎች በቀረበው የእቃ መግለጫ /specification / መሰረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል ፡፡
- ተጫራቾችማንኛውንም የመንግስትታክስና የግብር ግዴታዎች ከነመጓጓዣው ከሚያቀርቡበት ነጠላ ዋጋ ውስጥ አካተው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት በ10ኛው የስራ ቀን ከቀኑ 8፡00 ተዘግቶ 8፡ 30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮቁጥር 9 ይከፈታል፡፡ ዕለቱም በአል ወይም ዝግ ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተገለፀው ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾቹ በጨረታው ሲያሸንፉ 10% የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- በጨረታው አሸናፊ ድርጅት ውል ከፈረሙበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን እቃማንኛውንም የትራንስፖርት ወጪ በራሳቸው ችለው በት/ቤቱ ንብረት ክፍል ድረስ ገቢ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡
- ቢሮው ከጠቅላላ ግዥ 20% የመጨመር ወይም የመቀነስ መብት አለው፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡– 6 ኪሎ ከመነን ት/ቤት ከፍ ብሎ ወደ ሽሮ ሜዳ በሚወስደው
መንገድ ከወረዳ 3 አስተዳደር ጽ/ቤት ፊት ለፊት ይገኛል ፡፡
ስልክ ቁጥር፡– 0111-126-0975 ወይም 011-122-27-02/03
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በጉለሌ ክ/ከተማ
የወረዳ 3 ት/ጽ/ቤት የፀሐይ ጮራ የመጀ/ደ/ት/ቤት