ለሶስተኛ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የጮራ ወረዳ ገቢዎች ባለሥልጣን በታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 203/2009 አንቀጽ 43 ንዑስ አንቀጽ 9 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት የሀውስ ኢንተርናሸናል ፋይናንስና ኮንስትራክሽን ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ያለባቸውን የመንግስት ግብር መክፍል ባለመቻላቸው የማህበሩ ንብረት የሆኑ ተሽከርካሪዎች በዕዳ የያዛቸውን ከዚህ በታች የተዘረዘሩት፡
ተ.ቁ |
የተሽከርካሪው ዓይነት |
ሠሌዳ ቁጥር |
የሻንሲ ቁጥር |
የሞተር ቁጥር |
የሞዴል ቁጥር |
የጨረታ መነሻ ዋጋ ቀረጥ ሳይጨምር |
1 |
ሻወር ትራክ የጭነት |
3-63927 ኢት |
WJME3TRE2 DC259622 |
200278
|
AD380T38H |
1,738,012.89 |
2 |
ፒክአፕ ደብል |
3- A05807 ኢት |
MROFR22G oE0721840 |
2KD-s354820 |
KUN25LPRMDHV
|
1,246,934.85
|
በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ በዚሁ መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች ተወዳድራችሁ ሙግዛት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
የመወዳደሪያ መስፈርቶች:-
- የጨረታ ሰነዱ በቡኖ በደሌ ዞን በጮራ ወረዳ ገቢዎች ባለሥልጣን ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር አራት (4) በመገኘት የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ) በመክፈል ለእያንዳንዱ ተሽከርካሪ የተዘጋጀውን ሰነድ መግዛት የሚችል፡፡
- የተሽከርካሪዎቹን ሁኔታ ማየት የሚፈልግ ተጫራች በአጫራች መ/ቤት ቅጥር ግቢ በመገኘት ዘወትር በሥራ ሰዓት ማየት ይቻላል፡፡
- ተጫራች መግዛት የፈለገውን ተሽከርካሪለይተው በመጥቀስ ከጨረታ ሰነዱጋርተያይዘው በሚገኘው የዋጋ ማቅረቢያ ሠንጠረዥ የሚጫረቱበትን ዋጋ በመጥቀስ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማሸግ ማቅረብ የሚችል፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ከ29/8/2012 ዓ.ም እስከ 13/9/2012 ዓ.ም ለ15 ቀን የሚቆይ ሲሆን ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ እስከ ቀን 3/9/2012 ዓ.ም በሥራ ቀን እስከ 10፡30 ሰዓት ድረስ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአጫራች መ/ቤት ቢሮ ቁጥር አንድ (1 ) በ16/9/2012 ዓ.ም ስለሚከፈት ተጫራቾች የጨረታው ሰነድ በአጫራች መ/ቤት ቢሮ ቁጥር አንድ (1) በመገኘት ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ በማስገባት በዛኑ ቀን በ4፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱትን ተሽከርካሪ ለመግዛት ያስገቡት ዋጋ 15 % የጨረታው ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ በባንክ በተረጋገጠ ማዘዣ (CPO) በማስያዝ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዞ ማቅረብ አለበት፡፡
- *With Holding tax” (2 % ) አሸናፊው የሚከፍል ይሆናል፡፡
- አሸናፊው ተሽከርካሪውን ያሸነፈበትን ዋጋ በ5 ቀን ውስጥ ገንዘቡን ሙሉ በሙሉ በመክፈል ተሽከርካሪውን ተረክበው የማንሳት ግዴታ አለበት፡፡ በተጠቀሰው ቀን ካላነሳ ያስያዘው ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ሆኖ ተሽከርካሪው በድጋሚ ለጨረታ ይቀርባል፡፡
- ለተሽከርካሪው የሚያስፈልገው ማንኛውም የተለያዩ ወጪዎች የሚፈለግባቸው የመንግስት ቀረጥን ጨምሮ ሙሉ በሙሉ በአሸናፊው የሚሸፈን ይሆናል፡፡
- ባለሥልጣኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- ለተጨማሪ መረጃ የጮራ ወረዳ ገቢዎች ባለሥልጣን ጽ/ቤት ስልክ ቁጥር 0473370439 ወይም 0473370314 ደውለው መጠየቅ ይቻላሉ፡፡
በቡኖ በደሌ ዞን የጮራ ወረዳ ገቢዎች
ባስሥልጣን ጽ/ቤት