የጨረታ ማስታወቂያ
የጨፌ ኦሮሚያ ጽ/ቤት የተለያዩ ቁርጥራጭ ብረቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ፣
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ከጽ/ቤታችን አንደኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 18 ለዚህ የተዘጋጀውን ዶክሜንት መግዛት ይችላሉ፣
- ንብረቱን ዘወትር በሥራ ቀን 3፡00 – 10፡00 ሰዓት በጽ/ቤቱ በመገኘት መመልከት ይችላሉ፡፡
- የሚወዳደሩበትን ዝርዝር ዋጋ በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ ማስታወቂያው ከወጣበት እስከ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ አራት ሰዓት 4:00/ ድረስ ለዚሁ ግዢ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፣
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ በ4:30 ሰዓት ላይ ይከፈታል:: 16ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ፣ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል::
- ተጫራቾች ለመወዳደር ካቀረቡት ጠቅላላ ዋጋ 10% የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ /CPO/ ከዋጋ ማቅረቢያ ዶክሜንት ጋር ፖስታ ውስጥ በማስገባት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታውን ያሸነፉ ተወዳዳሪዎች አሸናፊነታቸው በደብዳቤ ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ እስከ አምስት ቀን ድረስ ብረቱን ከጽ/ቤቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ ማንሳት አለባቸው::
- ጽ/ቤቱ ሌላ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
አድራሻ፡– ሳር ቤት፣ አካባቢ ከኦሮሚያ ቢሮዎች ፊት ለፊት ወይም ከኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ ባቦ ቅርንጫፍ አጠገብ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0113 71 66 11 መጠየቅ ይቻላል፡፡
የጨፌ ኦሮሚያ ጽ/ቤት