የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር 001/2013
የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በምዕ/ሐረርጌ ዞን የጨርጨር ፖሊ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ በ2013 በጀት ዓመት ለየተለያዩ ት/ክፍሎች የሚውሉ ቋሚና አላቂ የቴክኒከና ሙያ የስልጠና እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ የሚከተለውን መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል።
- እቃውን በጥራት ለማቅረብ የሚያስችል ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ
- ተጫራቾች የተጨማሪ ዕሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢዎች ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች በአቅራቢዎች/በመስኩ ዝርዝር ውስጥ የተካተቱ መሆን እለባቸው።
- አቅራቢዎች ከአስመጪው ድርጅት ሰርተፍኬት (ጋራንት) ማቅረብ አለባቸው።
- የጨረታ ማስከበሪያ 5000 (አምስት ሺህ) ብር በባንከ በተረጋገጠ (CPO) ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማስያዝ አለበት፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ) በመክፈል ከላይ በተገለጸው የጽ/ቤቱ እድራሻ (ጭሮ ወይም አሰበ ተፈሪ ከተማ በኮሌጁ ፋይናንስ ቢሮ) በመቅረብ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት መግዛት ይቻላል።
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ዕለት እስከ 07/03/2013 ከቀኑ 4፡00 ሰአት ድረስ ለተጫራቾች ክፍት ይሆናል።
- ተጫራች የጨረታ ሰነዱን የሚጫረቱበትን መወዳደሪያ የአንዱን ዋጋ በመጥቀስ ስሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ውስጥ አድርጎ እስከ 07/03/2013 እስከ ቀኑ 2፡00 ሰዓት ድረስ ጭሮ ከተማ በኮሌጁ ፋይናንስ ቢሮ ገቢ ማድረግ አለባቸው። ጨረታው በዚሁ ዕለት ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ ከቀኑ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- አሸናፊው የጨረታ ተወዳዳሪ ማሸነፉ ከተገለጸለት በኋላ በአምስት (5) ቀናቶች ውስጥ ከግዢው ጠቅላላ ዋጋ ላይ 10% የውል ማስከበሪያ ማስያዝ አለበት።
- ለጨረታ ከቀረቡ ዕቃዎች ዝርዝር ውስጥ ኮሌጁ እስከ 20% ለመጨመር ወይም ለመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተወዳዳሪዎች በጨረታው ሰነድ በእያንዳንዱ ገጽ ላይ ማህተምና ፈርማቸውን ማኖር አለባቸው።
- ኮሌጁ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻችን፡– በም/ሐረ/ዞን ጨርጨር ፖሊ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ
ጭሮ/አሰበ ተፈሪ
0255510120/0944141498
የጨርጨር ፖሊቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ
ጭሮ/አሰበ ተፈሪ
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት
በምዕ/ሐረርጌ ዞን የጨርጨር
በምዕ/ሐረርጌ ዞን የጨርጨር
ፖሊ ቴክኒከና ሙያ ኮሌጅ