ተሽከርካሪዎች፣ የኮንስትራክሽን መሣሪያዎች፣ መለዋወጫ ዕቃዎች እና
ሌሎች ዕቃዎች ለመሸጥ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 02/2013
የጥቁር አባይ ኮንስትራክሽን ኣ/ማ/በሕግ በመፍረስ ላይ ያለ/በአዲስ አበባ ሳሪስ ማዕከላዊ ጋራዥ፣ ቃሊቲ አቃቂ፣በደቡብ ኦሞ ዞን ጂንካ ከተማ በነታ ቀበሌ፤ጊቤ ካምፕ፣ ጅማ እና በበደሌ ቢራ ፋብሪካ ውስጥ የሚገኙትን
- የተሽከርካሪዎች፣ የኮንስትራከሽን እና የወርክ ሾፕ መሣሪያዎች፣
- መለዋወጫ ዕቃዎች እና ሌሎች የተለያዩ ዕቃዎች ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም፡-
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመከፈል ሳሪስ ንፋስ ስልክ ቀለም ፋብሪካ አጠገብ ከሚገኘው የአ/ማህበሩ ቢሮ ቁጥር 8 የጨረታ ሰነዱን ማግኘት ይችላል፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ንብረቶች የጨረታ ሰነድ በመያዝ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከአዲስ አበባ ዋናው መ/ቤት ንብረት ክፍል የሚሰጠውን የመግቢያ ወረቀት በመያዝ መመልከት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ ከሚጫረቱበት ጠቅላላ ዋጋ አስር በመቶ (10%) በባንክ በተመሰከረለት ቼክ (ሲፒኦ) በድርጅቱ ትከክለኛ ስም /BLUE NILE CONSTRUCTION SHARE COM-PANY/ በማሰራትና ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ በፖስታው ላይ የተጫራቹን ስምና አድራሻ ስግልፅ በመፃፍ እስከ ጨረታው መዝጊያ ህዳር 22 ቀን 2013 ዓም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ በዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- በቂ የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond) ያላስያዙ ተጫራቾችን ኮሚቴው ከጨረታው ይሰርዛል፡፡
- የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያው ለተሸናፊዎች የጨረታው ውጤት እንደፀደቀ ተመላሽ የሚደረግ ሲሆን ለአሸናፊዎች ግን የገዙበትን ዋጋ አጠቃለው ከከፈሉ በኋላ ይሆናል፡፡
- የጨረታው አሸናፊዎች በውጤቱ መሠረት ክፍያ ከፈፀሙ በኋላ ያሸነፉባቸውን ንብረቶች በሚወጣው የማስረከቢያ ፕሮግራም መሠረት አንስተው ማጠናቀቅ አለባቸው፡፡ በፕሮግራሙ መሠረት ሳያነሱ ቢቀሩ ለሚፈጠረው ችግር መ/ቤቱ ተጠያቂ አይሆንም::
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአ/ማህበሩ መሰብሰቢያ አዳራሽ በዚሁ ቀን ኅዳር 22 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ይከፈታል፡፡
- ድርጅቱ ስለአሻሻጡ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ስልክ ቁጥር፡-011 4426332
የጥቁር ዓባይ ኮንስትራክሽን
አክሲዮን ማህበር