የጨረታ ማስታወቂያ
ጢስ አሳት ውሃ ስራዎች ኃ/ተ/የግ/ማህበር
የጢስ እሳት ውሃ ስራዎች ኃ/የተ/የግ/ማህበር ከታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ከእቅራቢዎች ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ተ.ቁ |
ሎት |
የእቃው አይነት |
1 |
ሎት 1 |
ኤሌክትሮ ሜካኒካል እቃዎች (ፓምፕና ጄኔሬተር) |
2 |
ሎት 2 |
የማሽነሪና ተሽከርካሪ መለዋወጫዎች |
3 |
ሎት 3 |
ስቲል ኤዚንግና የቁፋሮ ቢቶች |
4 |
ሎት 4 |
ኤሌክትሪካል ኬብል |
5 |
ሎት 5 |
የቅየሳ መሳሪያ |
ስለዚህ ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራና በጨረታዉ መሳተፍ የሚፈልግ አቅራቢ ድርጅት ዝርዝር የጨረታ ሰነዱን ባህርዳር ከተማ ከሚገኘው አባይ ማዶ ቴዲ የአሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ ጎን ኩባንያች ጽ/ቤት ማግኘት ይችላል።
የተጫራቾች መመሪያ፡-
- ተጫራቾች የዘመኑን ግብር ከፍለው የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ እና የTIN ሰርተፊኬት፣ በዘርፉ ለመሰማራት የተሰጣቸውን ፈቃድ እና ተያያዥነት ያላቸውን የመልካም ስራ አፈፃፀም ማስረጃዎች ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ጨረታው ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ21ኛው ቀን ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከቀኑ 10፡30 ሰዓት ባህርዳር ከተማ አባይ ማዶ ቴዲ የእሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ ጎን በሚገኘው ዋናው መ/ቤት ተጫራቾች እና ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት ተዘግቶ ይከፈታል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በድርጅታችን ድህረ–ገፅ WWW.TSISAT.COM ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ዋስትና ለአንድ ሎት 30,00.00 ብር በ C.P.O ወይም ያለቅድመ ሁኔታ እንደተጠየቀ ለገዥ ሚከፈል (unconditional Bank Guarantee) ማስያዝ አለባቸው።
- ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያቸውን እና ቴክኒካል ሰነዳቸውን ለየብቻ በተለያየ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ተጫራች ድርጅቶች ለሚያቀርቡት ዋጋ ለእያንዳንዱ እቃ ነጠላ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ በትክክል ሞልተው በግልፅ ማስቀመጥ እለባቸው።
- ይህ ጨረታ በኩባንያችን የግዥ መመሪያ ሚያዝያ/2009/ መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡
- ኩባንያው በጨረታ ሰነዱ ላይ ከተገለፀው መጠን 20% ቢጨምር ወይም ሲቀንስ የጨረታ አሸናፊው ውል የመያዝ ግዴታ ይኖርበታል።
- የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ በጽሁፍ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ10 ቀናት ውስጥ የጠቅላላ ዋጋውን 10 % የውል ማስከበሪያ ያለቅድመ ሁኔታ ለግዥ የሚከፈል (unconditional Bank Guarantee) በማሰራት ውል የመያዝ ግዴታ ይኖርበታል።
- የማቅረቢያ ጊዜ 30-45 ቀን መሆን አለበት። የአቅራቢዎች ዋጋ ቢያንስ ለ90 ቀናት ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ፀንቶ መቆየት አለበት።
- ኩባንያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ በዚህ ጨረታ አይገደድም ወይም ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ማሳሰቢያ፡– ውድድሩ የሚካሄደው በሎት ሳይሆን በእያንዳንዷ እቃ ነጠላ ዋጋ በሚሞሉት ዋጋ መሰረት ይሆናል፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥራችን፡-058-220-48-26 /0583202548
በፋክስ ቁጥራችን 0582204830 መጠየቅ ይችላሉ።
ጢስ እሳት ውሃ ስራዎች ኃ/የተ/የግ/ ማህበር፣ ባህር ዳር