የጨረታ ማስታወቂያ
የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ለ2013 በጀት አመት አገልግሎት የሚውል ፦
- የሰራተኞች ደንብ ልብስ ግዥ ጨረታ ቁጥር 04/2013 በግልጽ ጨረታ መስፈርቱን በሚያሟሉ እና በዘርፉ ሕጋዊ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል ::
በዚሁ መሰረት በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች፡-
- በዘርፉ ህጋዊና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ::
- በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጄንሲ አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ሕጋዊ የአቅራቢዎች ምዝገባ ፈቃድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ::
- ከአቅራቢዎች ስም ዝርዝር ውስጥ በተለያዩ ጥፋቶች ያልተሰረዙ ወይም የቅጣት ግዚያቸው ያልተጠናቀቀ በዚህ ጨረታ ላይ መሳተፍ አይችሉም::
- በገንዘብ ሚ/ር በዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር በተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ እንዲሁም 2013 ዓ.ም በጨረታ መሳተፍ የሚችሉ መሆናቸው ከሚመለከተው ግብር ሰብሳቢ አካል የተሰጣቸውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የስራ ቀናት ክፍት ሆኖ ይቆያል፡፡
- ተጫራቾች ዋጋ ሞልተው የሚያቀርቡበት ከጨረታ ሰነድ ጋር ተያይዞ በቀረበው የዋጋ ማቅረቢያ ቫትን ጨምሮ በቀረበው ቅጽ ብቻ ይሆናል::
- እያንዳንዱ ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ለሚወዳደሩበት የጠቅላላ ዋጋ /VAT/ጨምሮ ብር 2% በባንክ በተረጋገጠ ዋስትና ሲፒኦ ወይም የባንክ ጋራንቲ በጽ/ቤቱ ስም ማሲያዝ ይኖርበታል፡፡
- የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 100/አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት የግዥና ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 305 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
- እያንዳንዱ ተጫራች ቴክኒካል እና ፋይናሻል ዶክመንት በተለያየ ፖስታ ታሽጎ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- እያንዳንዱ ተጫራች ለሚወዳደርባቸው የሰራተኞች ደንብ ልብስ ናሙና አይነት ጨረታው ከመከፈቱ ከአንድ ቀን በፊት የማቅረብ ግዴታ አለበት ::
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጥር 14 ቀን 2013 ዓ.ም ከሰዓት 8:00 ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከሰዓት 8:30 ይከፈታል ::
- ጨረታውን ያሸነፈ ተጫራች ዕቃውን እስከ ጽ/ቤቱ ድረስ በራሱ ትራንስፖርት ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
የጠቅላይ ሚ/ር ጽ/ቤት