ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ት/ት/ጽ/ቤት የጠመንጃ ያዥ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ለ 2013 ዓ.ም በጀት አመት አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ፡-
- ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች
- አላቂ የጽዳት ዕቃዎች
- አላቂ የት/ት መርጃ መሣሪያዎች
- የሰራተኞች የደንብ ልብስ
- የተጨማሪ እሴት ታክስ / ቫት /ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ እና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- የጨረታ ማስከበሪያ 3000(ሶስት ሺ ብር) በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 50 (ሃምሳ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናቶች በጠመንጃ ያዥ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 6 በግንባር በመቅረብ መግዛት ይችላሉ ::
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዕቃ ናሙና ጨረታው ከመከፈቱ 1 ቀን በፊት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል መጫረት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው በ10ኛው ቀን ከቀኑ 11.00 ተዘግቶ / ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ከሆነ/ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በትምህርት ቤቱ ፋይናንስ ቢሮ ይከፈታል::
- አሸናፊዎች ያሸነፉባቸውን ዕቃዎች ትምህርት ቤቱ ግምጃ ቤት ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ትምህርት ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- የተሰረዘ የተደለዘ ግልጽነት የሌለው ጨረታ ሰነድ ውድቅ ይሆናል፡፡
ለበለጠ መረጃ፡– ስልክ ቁጥር 0114-703882
አድራሻ፡– ደብረዘይት መንገድ በጠመንጃ ያዥ ንግድ ባንክ ፊትለፊት በእምነት ሬስቶራንት ጀርባ 200 ሜትር ወደ ውስጥ ገባ ብሎ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት
ቢሮ ያቂርቆስ ክፍስ ከተማ ትምህርት ጽ/
ቤቱ የጠመንጃ ያዥ የመጀ/ደ/ት/ቤት