የግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ የ2013 ዓ.ም
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 001/2013 ዓ.ም
የጎፋ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
- ሎት– 1 የኤሌክትሪክ ዕቃዎች – —————-5000
- ሎት– 2 የማኑፋክቸሪንግ(ብረታ ብረት) ዕቃዎች ——5000
- ሎት– 3 የጋርመንት ዕቃዎች——————–5000
- ሎት– 4 የኮንስትራክሽን ዕቃዎች —————–5000
- ሎት– 5 የአውቶሞቲቭ ዕቃዎች——————-5000
- ሎት– 6 ኮምፒውተርና ተጓዳኝ ዕቃዎች—————— 5000
- ሎት– 7 የፅህፈት ዕቃዎች ———————-3000
- ሎት– 8 አላቂ የፅዳት ዕቃዎችና የጸጉር ቤት ዕቃዎች—-2000
- ሎት– 9 የደንብ ልብስ ዕቃዎች ——————4000
- ሎት-10 የፈርኒቸር ዕቃዎች ——————–5000
- ሎት– 11 የህትመት ሥራዎች ——————-2000
ከላይ ያሉትን የግዥ አይነቶች መሰረት በማድረግ በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች
- ለሚጫረቱበት ዘርፍ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው:: የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆናቸው የሚገልጽ ማረጋገጫ፣ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የምዝገባ ሰርተፊኬት እና በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ መመዝገባቸው የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የጨረታው ሰነድ የማይመለስ ብር 100/ አንድ መቶ ብር / በመክፈል ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10/አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ በስራ ሰዓት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡00 በኮሌጁ የመንግስት ግዥ አስተዳደር ቡድን መሪ ቢሮ ቁጥር 19 በመቅረብ መውሰድ ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዕቃ ኮሌጁ ባስቀመጠው ሎት መሰረት ዋጋቸውን በመሙላት የጽህፈት እቃዎችን፣ የፅዳት እቃዎች እና የደንብ ልብስ እቃዎችን ብቻ ቅድሚያ ሳምፕል በማቅረብ በየሎቱ በፖስታ በማሸግና በግልፅ በመጻፍ ኦርጅናልና አንድ ፎቶ ኮፒ ሰርተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ዋጋ ሲሞላ በኮሌጁ ኦርጅናል ሰነድ ላይ መሆን አለበት፡፡
- ዋጋው ከነቫቱ መሞላት አለበት፡፡
- ጥቃቅንና አነስተኛ ተወዳዳሪዎች ከአደራጃችሁ ተቋም በኮሌጁ ስም ደብዳቤ መቅረብ አለበት፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ከላይ በየሎቱ በተገለጸው መሰረተ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ /CPO/ ከጨረታ ነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- አሸናፊ ተጫራቾች የአሸናፊ ደብዳቤ ከደረሳቸው ጀምሮ ባሉት 7/ሰባት/ ቀናት ውስጥ የቅሬታ ማቅረቢያ ቀናትን ሳይጨምር ያሽነፉበትን እቃ ወይም አገልግሎት ጠቅላላ ዋጋ 10/አስር/ፐርሰንት የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- በጨረታ አሸናፊ የሆነ ድርጅት ያሸነፈበትን ንብረት በራሱ የትራንስፖርት ወጪ በኮሌጁ ንብረት ክፍል ግቢ ማድረግ ይኖርበታል፡፡
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በወጣ በ11ኛው የስራ ቀናት 4፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥን ተዘግቶ በዛው ቀን በ4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮሌጁ ላይብረሪ ይከፈታል፡፡ የጨረታ መክፈቻ ቀኑ በስራ ቀን ያልዋለ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ኮሌጁ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ እንዲሁም ከቀረቡት ዝርዝሮች ውስጥ 20 ፐርሰንት ብዛት ለመጨመር/ ለመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው::
አድራሻ፡– ን/ስ/ላ ጎፋ ካምፕ ወረዳ 5 ልዩ ስሙ የድሮ ገና ት/ቤት ከ20ቴ/ሙ/ማ/ተቋም በአሁኑ ጎፋ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ
ስልክ ቁጥር፡– 011-4-70-41-50 ፤ 011-4-66-61-12 እና 0114-162-874
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቴ/ሙ/ትምህርትና ስልጠና ቢሮ
የጎፋ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ