ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በባህር ዳርና አካባቢዋ ከፍተኛ ፍ/ቤት የጎ/ቆ/ወ/ፍ/ቤት በ2013 በጀት ዓመት ለአገልግሎት የሚውል አላቂና ቋሚ የቢሮና የቤት እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ማለትም
- ሎት 1 የጽህፈት መሣሪያ፣
- ሎት 2 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣
- ሎት 3 ህትመት፣
- ሎት 4 የጽዳት እቃዎች፣
- ሎት 5 ብትን ልብስ
- ሎት 6 ጫማ
- ሎት 7 የተዘጋጁ ልብሶች
- ሎት 8 የቤትና የቢሮ እቃዎች
- ሎት 9 የውጭ ፈርኒቸር
- ሎት 10 የህንፃ መሣሪያዎች አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ መወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ድርጅት መጫረት የሚችል መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣
- የድርጅቱ ህጋዊ ማህተም ያላቸው፣
- የግብር ከፋይ ቲን ያላቸው፣
- የግዥው መጠን ከ200 ሺህ ብር እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም ቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጫራቾች ለመሣተፍ ከላይ ከ 1 እስከ 3 የተጠቀሱትን መረጃዎች ፎቶ ኮፒ አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚገዙ እቃዎች ዓይነት ወይም እስፔስፊኬሽን ዝርዝር መግለጫ በጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 25 በመክፈል ቢሮ ቁጥር 11 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት የግዥው ጠቅላላ ዋጋ 1 በመቶ በሲፒኦ/በጥሬ ገንዘብ/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ አሸናፊ ድርጅቱ ከተገለፀ በኋላ የውል ማስከበሪያ የጠቅላላው ዋጋ 10 መቶ በሲፒኦ/በጥሬ ገንዘብ/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በአንድ ወጥ በታሸገ ፖስታ በጎ/ቆ/ወ/ፍ/ቤት በግ/ፋይ/ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 11 ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- መ/ቤቱ እቃዎችን 20 በመቶ መጨመር ወይም መቀነስ ይችላል፡፡ ለእያንዳንዱ እቃዎች ናሙና ሣምፕል ከተቋሙ በአካል በመምጣት ማየትና መሙላት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ከ02/02/2013 ዓ/ም እስከ 16/02/2013 ዓ/ም 11፡30 ድረስ መግዛት ይችላል፡፡
- በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ከ02/02/2013 ዓ/ም እስከ 16/02/2013 ዓ/ም ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 11 ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 17/02/2013 ዓ/ም እስከ 3፡00 ማስገባት ይችላሉ፡፡ በ3፡05 ታሽጐ 3፡30 ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈውን እቃ ከመ/ቤቱ ወይም ጎ/ቆ/ወ/ፍ/ቤት ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት፡፡
- ከጨረታ ሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም ሆኖ ስርዝ ድልዝ ካለ መስተካከሉን ፓራፍ መደረግ አለበት፡፡
- ጨረታው የሚዘጋበት የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣይ የስራ ቀን ይከፈታል፡፡
- ውድድሩ የሚካሄድ በሎት ዋጋ ነው፡፡
- በጨረታው መሣተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 058 5567904 ወይም 0962723610 መደወል ይችላሉ፡፡
- ከዚህ በላይ ያልተጠቀሱ የጨረታ መመሪያዎች በግዥ መመሪያ ቁጥር 1/2003 መሰረት ተግባራዊ የሚደርጉ ይሆናል፡፡
የጎንጅ ቆለላ ወ/ፍ/ቤት