ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የጎንደር ከተማ አስተዳደር ገን/ኢኮ/ትብብር መምሪያ በጎንደር ከተማ አስ/ባ/ቱ/ስ/መምሪያ ስር ለሚገኘው የካሜሎት መዝናኛ ቤት የጥገና ስራ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡ ስለዚህ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን አያገስፅን፡ማቅረብ የምትችሉት መረጃ፡
- የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸሁ ፡፡
- የዘመኑን ግብር ለመከፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TiN/ ያላቸው፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
- ከደረጃ 1 እስከ ደረጃ 3 ፈቃድ ያላቸው ፡፡
- ተጫራቶች ከላይ ከተራ ቁጥር 1-5 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጥገናውን ዝርዝር መግለጫ /የስራ ዝርዝር ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ ፡፡
- ተጫራቶች ለጨረታ ማስከበሪያ/ ቢድ ቦንድ/ ከሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ ላይ 1% በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 50 /ሃምሳ ብር/ በመክፈል ጎን/ከ/አስ/ገ/ኢኮ/ትብብር መምሪያ ቢሮ ቁጥር 11 መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሃሳባቸውን አንድ ወጥ በሆኑ ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በመሙላት በታሸገ ፖስታ በጎ/ከ/አስ/ግዥና/ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 7 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በአየር ላይ የሚቆይበት ጊዜ ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት የሚቆይ ሲሆን በ15ኛው ቀን እስከ ቀኑ 11፡30 ሰዓት ድረስ በጎንደር ከ/አስ/ገን/ኢኮ/ትብብር መምሪያ ቢሮ ቁጥር 1 በመምጣት የጨረታ ሰነድ መግዛት የሚችሉ ሲሆን ጨረታው በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ጨረታው በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቶች ዋጋውን በሚሞሉበት ወቅት ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም፡፡
- ተጫራቶች በሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ሙሉ ስምና ፊርማቸውን የድርጅቱን ማህተም ማድረግ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የሚቀርብ ቅሬታ ካለ ጨረታው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 5 የስራ ቀን ማቅረብ የሚችሉ ሲሆን ከ5 የስራ ቀናት በኋላ የሚቀርብ ቅሬታ የማንቀበል መሆኑን እንገልፃለን።
- ለተጨማሪ መረጃ ካስፈለገ ጎን/ከተ/አስ/ገን/አካ/ት/ብ/መምሪያ ቢሮ ቁጥር 07 በአካል በመምጣት ወይም በስልክ ቁጥር-058 126 03 06 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የጎንደር ከተማ አስተዳደር ገን/ኢኮ/
ትብብር መምሪያ በጎንደር ከተማ
አስ/ባ/ቱ/ስ/መምሪያ