ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጎንደር ከተማ አስተዳደር ገን/ኢኮ/ትብብር መምሪያ ለ2013 የበጀት አመት በከተማ አስተዳደሩ ለሚተዳደሩ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል
- በሎት 1 የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች
- በሎት 2 የመኪና መለዋወጫ
- በሎት 3 ፒፒሲ ሲሚንቶ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እየገለፅን ማቅረብ የምትችሉት መረጃ፡
- የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላችሁ
- የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው
- የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
- ተጫራቾች ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ከሎት 1 እስከ ሎት 4 የቀረቡትን ዕቃዎች ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ /ቢድ ቦንድ/ ከሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ ላይ 1% በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 50/ሃምሳ ብር/ በመክፈል ገ/አካ/ኢ/ትብብር መምሪያ ቢሮ ቁጥር 11 መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሃሳባቸውን አንድ ወጥ በሆኑ ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በመሙላት በታሸገ ፖስታ በጎ/ከ/አስ/ግዥና/ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 7 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በአየር ላይ የሚቆይበት ጊዜ ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት የሚቆይ ሲሆን በ15ኛው ቀን እስከ 11፡30 ሰዓት ድረስ በጎንደር ከ/አስ/ገን/ኢኮ/ትብብር/መምሪያ ቢሮ ቁጥር 11 በመምጣት የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡ ጨረታው በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ዋጋውን በሚሞሉበት ወቅት ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም፡፡
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ሙሉ ስምና ፊርማቸውን የድርጅቱን ማህተም ማድረግ አለባቸው
- ማንኛውም ተጫራች የሚቀርብ ቅሬታ ካለ ጨረታው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 5 የስራ ቀን ማቅረብ የሚችሉ ሲሆን ከ5 የስራ ቀናት በኋላ የሚቀርብ ቅሬታ የማንቀበል መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- ለተጨማሪ መረጃ ካስፈለገ ጎን/ከተ/አስ/ገን/አካ/ትብ/መምሪያ ቢሮ ቁጥር 07 በአካል በመምጣት ወይም በስልክ ቁጥር 058 126 03 06 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡
- ዕቃውን በሚፈለግበት ወቅት ጎን/ከ/አስ/ገ/አካ/ኢኮ/ትብብር መምሪያ ድረስ ማቅረብ የሚችል::
- ተጫራቾች መጫረት/መወዳደር/የሚችሉት በሚመለከታቸው የንግድ ዘርፍ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ለውድድር ሲቀርቡ ኦርጅናል የንግድ ፈቃድ ፣ ቲን ነምበር ቫት ምዝገባ ሰርተፍኬት ይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ማሳሰቢያ
- አሸናፊው ተጫራች የሚያቀርበው ዕቃ ኦርጅናልና ጥራቱን የጠበቀ እና በወጣው እስፔስፊኬሽን እንዲሁም በቀረበው ናሙና መሰረት ይሆናል።
- የሚፈጸመው ግዥ ከበጀት አንጻር ሊቀንስ ወይም ሊጨምር የሚችል መሆኑን፡፡
- አሸናፊው የሚለየው በእያንዳንዱ ሎት ጠቅላላ ዋጋ ይሆናል፡፡
- ከተዘረዘሩት ዕቃዎች ውስጥ አንዱን ያልሞላ ከውድድር ውጪ ይሆናል፡፡
ፖሳቁ፡ 192፣ ስልክ ቁጥር 0581-26-03-06
ፋክስ፡– 0581-11-75-63
Email: gontipco@ethionet.et
የጎንደር ከተማ አስተዳደር ገን/ኢኮ/ትብብር መምሪያ