Land Lease & Real Estate

የጎብጎብ ከተማ ን/ማዘጋጃ ቤት ለ1ኛ ዙር ጨረታ ለመኖሪያ ብዛት 1 ለድርጅት 2 ቅይጥ ብዛት 1 እና አጠቃላይ 4 ቦታዎችን በጨረታ ለተጠቃሚዎች ማስተላለፍ ይፈልጋል

የሊዝ የጨረታ ማስታወቂያ

በደቡብ ጐንደር ዞን በላይ ጋይንት ወረዳ የጎብጎብ ከተማ ን/ማዘጋጃ ቤት ከተማ ልማት ጽ/ቤቶችና ኮንስትራክሽን አገልግሎት ጽ/ቤት የከተማ ቦታን በሊዝ ለመያዝ የሚደነግገውን አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀጽ 5/1 መሰረት በ2012 በጀት ዓመት ለ1ኛ ዙር ጨረታ ለመኖሪያ ብዛት 1 ለድርጅት 2 ቅይጥ ብዛት 1 እና አጠቃላይ 4 ቦታዎችን በጨረታ ለተጠቃሚዎች ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም፡-

  1. መጫረት የሚፈልግ ማንኛውም ሰው/ግለሰብ/ ወይም ድርጅት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ቀናት ውስጥ የቦታውን ዝርዝር መረጃ እና የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ድርጅት ብር 200 ለመኖሪያና ለቅይጥ ብር 80 በመክፈል ቢሮ ቁጥር 3 በመምጣት መግዛት ይችላሉ፡፡
  2. የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ጊዜ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የስራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ ምሽቱ 11፡30 ብቻ በዚህ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ በቢሮ ቁጥር 3 ማስገባት ይችላሉ፡፡
  3.  ጨረታው የሚዘጋው በ10ኛው ቀን በ11፡30 ይሆናል፡፡
  4. ጨረታው የሚከፈተው ከተዘጋበት ቀን ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን በ3፡00 ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ካልሆነም ተወካዮቹም ሆነ ግለሰቦቹ ባይገኙም ጨረታው የሚከፈት ሲሆን ጨረታው የሚከፈትበት ቦታ በተመለከተ በጎብጎብ ከተማ ን/ማዘጋጃ ቤት ጽ/ቤት ይሆናል፡፡
  5. ይህ ማስታወቂያ ተግባራዊ የሚሆነው ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀን ይሆናል፡፡
  6. ለጨረታው ዝርዝር ሁኔታ በጽ/ቤቱ የማስታወቂያ ሰሌዳ ወይም በስልክ ቁጥር 058 295 0004 ደውሎ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ሌሎች ተጨማሪ ዝርዝር ሃሣቦችን ህጎችን ከሚሸጠው ሰነድ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  8. መ/ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የጎብጎብ ከተማ ን/ማዘጋጃ ቤት