Bid Closing Date: Sep 3, 2019 09:30 AM
የጨረታ ቁጥር MWD/36/76/2011
በባሌ ዞን የጎባ ከተማ ገ/ኢ/ል/ት/ጽ/ቤት በ2012 ዓ.ም በጀት 1ኛ ዙር ግዥ በከተማው ላሉ መ/ቤቶ የሚያገለግሉ፡-
- አላቂ እና ቋሚ እቃዎችን፣
- የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን፣
- ፈርኒቸሮች፣
- የቢሮ እቃዎች፣
- የከባድ እና ቀላል መኪና ጥገና እና እስፔርፓርት መለዋወጫ ፣
- ጎማዎች፣
- የኮምፒዩተር ጥገና፣
- የሰራተኛ ደምብ ልብሶችን፣
- የህትመት አይነቶችን፣
- እንዲሁም የምግብ ዓይነቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት እና ለማስጠገን እንዲሁም ለማሳተም ይፈልጋል፡፡
ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች
- Tin No ተመዝጋቢ መሆኑንና የዘመኑን ግብር የከፈለበትን ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና ፎቶ ኮፒውን ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ የሚችል፡፡
- ከላይ የተጠቀሱትን የውድድር ዓይነቶች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ /CPO/ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ 100.00 /አንድ መቶ/ ብር በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ Acc.No 1000028126712 በማስገባት ከጎባ ከተማ ገ/ኢ/ል/ት/ጽ/ቤት ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋናውንና ኮፒውን በተለያየ ፖስታ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት የስራ ቀን በ16ኛው ማለትም በ28/12/2011 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት የጨረታው ሰነድ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ገብቶ ከታሸገ በኋላ በዚሁ ቀን በ4፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎች የመጓጓዣ ሂሳብ ችሎ በገ/ኢ/ል/ት/ጽ/ቤት ንብረት ክፍል ገቢ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡
- የእቃዎቹን ዋጋ መ/ቤቱ የሚከፍለው ንብረቱን ሙሉ በሙሉ ንብረት ክፍል ገቢ ሆኖ በጥያቄው መሰረት መቅረቡ ሲረጋገጥ ብቻ ነው፡፡
- ተጫራቾች በቀረበው እስፔሲፊኬሽን መሰረት ጨረታውን ማሸነፋቸውን በደብዳቤ ከተገለፀላቸው ከ5 ቀን በኋላ በመስሪያ ቤቱ ቀርቦ ውል መፈራረም ይኖርባቸዋል፡፡ በተጨማሪም ውል ከገቡ በኋላ በ10 ቀን እቃውን ማስገባት አለባቸው፡፡
- እቃዎቹ ገቢ ሆነው ገንዘብ ከተከፈለ በኋላ ለአላቂ እቃዎች 6 ወር ለቋሚ እቃዎች 1ዓመት ጊዜ ጋራንት /ዋስትና/ መስጠት የሚችልና እቃዎቹ የተበላሹና ኦርጅናል ካልሆኑ ለመመለስ ግዴታ የሚገባ መሆን አለበት፡፡ እንዲሁም ናሙና ማቅረብ የሚችል ሲሆን ሰነድ ላይ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም፡፡
- ተጫራቾች ለጽሕፈት፣ ለኤሌክትሮኒክስ፣ ለጽዳትና ለቢሮ እቃዎች ፣ ለቋሚና ለአላቂ እቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000 /አስር ሺህ/ ብር በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ /CPO/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- አሸናፊ አቅራቢዎች የውል ማስከበሪያ የእቃውን ሙሉ ዋጋ 10% በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ /CPO/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- የእንጨት ውጤቶች የህትመት የደንብ ልብስ የምግብ እና የጥገና ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 3,000 /ሶስት ሺህ/ ብር በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ / CPO/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- በተራ ቁጥር 10 የተዘረዘሩትን እቃዎች ለማቅረብ የምትጫረቱ ተጫራቾች የምስክር ወረቀት ፎቶ ኮፒ ከሰነዱ ጋር ማያያዝ ይኖርባችኋል፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለበለጠ መረጃ ጎባ ከተማ ገ/ኢ/ል/ት/ጽ/ቤት በስልክ ቁጥር 0226612764 ይደውሉ፡፡
በኦሮሚያ ክልል በባሌ ዞን የጎባ ከተማ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት