የጨረታ ማስታወቂያ
የግዮን ሆቴል ድርጅት የሣባ አዳራሽ ግንባታ ሥራን ተጫራቾችን አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን ነጥቦች በማሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡
- የ2012 የታደሰ የንግድ ፈቃድ ሰርተፍኬት ያለው፡፡
- የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት ያለው፡፡
- Tin No. /የግብር መለያ ቁጥር/ ሰርተፍኬት ያለው፡፡
- /Vat/ ተጨማሪ እሴት ታክስ/ ሰርተፍኬት ያለው፡፡
- የታክስ ክሊራንስ 6 ወር ያልሆነው ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል፡፡
- የሥራና ከተማ ልማት ሚኒስቴር የተመዘገበና የ2012 የታደሰ የሥራ ፈቃድ ያለው፡፡
- ደረጃ BC4/GC5 እና ከዚያ በላይ የሆነ፡፡
- ተጫራቾች በፌዴራል ግዥ እና የመንግሥት ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በአቅራቢነት የተመዘገቡ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተመሰከረ ቼክ ወይም ሲፒኑ 125,000.00 /አንድ መቶ ሃያ አምስት ሺ ብር/ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- በጨረታው ሰነድ ላይ የተገለጹትን ፎርሞች ማሟላት የተጫራች ግዴት ሲሆን፤ ያልተሞላ የጨረታ ሰነድ ከውድድሩ የሚያስወጣ መሆኑን ተጫራቾች መገንዘብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታውን የሚያሸንፍ የሥራ ተቋራጭ ለሥራው ዋስትና 10 በመቶ Performance Bond/ እና የባንክ ዋስትና /Bank Guaranty/ ከባንክ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- የጨረታው ሰነድ በግልፅ ኦርጅናልና አንድ ኮፒ ተለይቶ የቴክኒክ፣ የፋይናንሺያልና ሲፒኦ /ቢድ ቦንድ/ ሰነዶች ለየብቻቸው በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ሙሉ አድራሻ፣ ቀን፣ ማህተም እና ፊርማ በማድረግ ታሽገው ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት ኦርጅናል ሆነ ኮፒ ሰነድ ነጠላ ዋጋ ላይ የማይነበብና ስርዝ ድልዝ ያለው መሆን የለበትም፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው መክፈቻ የዋጋ ንባብና በሂሳብ ማስተካከያ መሀል ያለው ልዩነት ከ2% መብለጥ የለበትም፡፡
- የጨረታ ሰነዱ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10 ተከታታይ የሥራ ቀን ድረስ በድርጅቱ የግዥ አገልግሎት ቢሮ ድረስ መተው መውሰድ ይችላሉ፡፡
- የጨረታውን ሳጥን የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት በ10ኛው ቀን ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚያው ዕለት ከቀኑ በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
ማሳሰቢያ፡
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡– 011 5 51 32 22 Ext. 5429/5163 ደውለው መጠየቅ ይቻላል፡፡
የሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ ሐሙስ ጠዋት ከ2፡00-6፡00 ከሰዓት በኋላ ከቀኑ 7፡00-11፡00 ዓርብ ጠዋት ከ2፡00 – 5፡30 ከሰዓት ከ7፡30 – 11፡00
ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ ለመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የግዮን ሆቴል ድርጅት