ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር 002/2013
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የግብርና ቢሮ የምዕራብ ጎጃም ዞን ግብርና መምሪያ የግብዓት ገጠር ፋይናንስ አቅርቦት ቡድን ለ2013/2014 የምርት ዘመን አገልግሎት የሚውል
- የኤን ፒ ኤስ ቦሮን እና ዩሪያ በድምሩ 901839 /ዘጠኝ መቶ አንድ ሺህ ስምንት መቶ ሰላሳ ዘጠኝ ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ በዞናችን ባለ1 ዮኒየን በሥሩ ባሉ መሠረታዊ ማኅበራት መጋዘን ድረስ ለመጓጓዝ ብቃት ያላቸውን የትራንስፖርት ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ በማወዳደር ውል ከተፈፀመበት ቀን እስከ ሀምሌ 30 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ ባለው ጊዜ የሚቆይ የትራንስፖርት አገልግሎት ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።
ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው ግዴታዎች።
- የዘመኑ የታደሰ ንግድ ሥራ ፈቃድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፣
- የግብር ከፋይነት ምዝገባ ሰርተፊኬት /ቲን/ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢነት ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፣
- በጨረታው የሚሣተፉ ተጫራቶች ከ70 ኩንታል በላይ የሚጭኑ ተሽከሪካሪዎች የሚያቀርቡ ከሆነ ከፌዴራል ትራንስፖርት ባለሥልጣን ተመዝግበው የተደራጁ ሆነው በዘመኑ የታደሠ የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፣
- እንዲሁም ተጫራቾች የሚያቀርቡት ከ70 ኩንታል በታች ከሆነ በክልል ትራንስፖርት ቢሮ ተመዝግበው የተደራጁ ሆነው በዘመኑ የታደሠ የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፣
- የተሽከርካሪ ዝርዝር ተቁ፣ የሴሌዳ ቁጥር፣ የመኪናው ዓይነትና የመጫን አቅም የሚያስረዳ ከፌዴራል ትራንስፖርት ባለሥልጣን ወይም ከክልል መንገድ ትራንስፖርት ቢሮ የተሰጠ የ2013 ዓ.ም ወቅታዊ የታደሠ ምዝገባ ፈቃድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፤
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር ከ 1 እስከ 5 የተጠቀሰውንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ማቅረብ አለባቸው፣
- የሚጓዘውን የአፈር ማዳበሪያ ዓይነት፣ መጠን ርቀት በኪሎ ሜትር ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፣
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100,00 /አንድ መቶ ብር/ በመከፈል ምዕ/ጎጃም ዞን ግብርና መምሪያ ማግኘት ይችላሉ፣
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት የአገልግሎቱን ጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታዎች ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ፖስታ በሚወዳደሩበት ሁ/የገ/ህ/ስ/ ዩኒየን ስም ማስያዝ አለባቸው።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሠነዱን በአንድ ፖስታ ከዋጋ ማቅረቢያ ጋር በማሸግ በአብክመ ግብርና ቢሮ የምዕራብ ጎጃም ዞን ግብርና ማስረጃ መምሪያ በግብ/ግብአት ገጠር ፋይናንሰ አቅ ቡድን ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ማሰታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ሠነዱን በሳጥኑ ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።የጨረታ ሳጥኑ የሚከፈተው በእለቱ በ4:30 በመምሪያው ግቢ በሚዘጋጅ ቦታ ይከፈታል። ዕለቱ በዓል ወይም ቅዳሜ እና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል፡፡
- መምሪያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በግብርና መምሪያው ግ/አ/ገ/ፋ ቢሮ ድረስ በአካል በመገኘት
ወይም በፋክስ ቁጥር 0587750881 በመላክ ወይም በስልክ ቁጥር 0587750871 በመደወል ማግኘት ይቻላል፡፡
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ግብርና
ቢሮ የምዕራብ ጎጃም ዞን ግብርና መምሪያ
ፍ/ሠላም