Building and Finishing Materials / Computer and Accessories / Equipment and Accessories / Materials / Motorcycles and Bicycles Purchase / Office Furniture / Office Machines and Accessories / Stationery / Tri Wheeler

የግራዋ ወረዳ ገንዘብና ትብብር ጽ/ቤት የሚያገለግሉ አላቂ የጽሕፈት መሣሪያዎች፣ ዕቃዎች፣ ቋሚ ዕቃዎች፣ የግንባታ መሣሪያዎች፣ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና መሣሪያዎች ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ የመኪናና የሞተር ሳይክሎች ጎማዎች፣ በወረዳው ለሚገኙ ሴክተር መሥሪያ ቤቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

የጨረታ ማስታወቂያ

በምሥራቅ ሐረርጌ ዞን የግራዋ ወረዳ ገንዘብና ትብብር /ቤት፤ 2013 . የበጀት ዓመት የሚያገለግሉ

 • አላቂ የጽሕፈት መሣሪያዎች ዕቃዎች፣
 • ቋሚ ዕቃዎች፣
 • የግንባታ መሣሪያዎች፣
 • የቴክኒክና ሙያ ስልጠና መሣሪያዎች ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣
 • የመኪናና የሞተር ሳይክሎች ጎማዎች፣ በወረዳው ለሚገኙ ሴክተር መሥሪያ ቤቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እናስታውቃለን፡፡

 1. ተጫራቾች ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ 2013 . ግብር አጠናቅቀው የከፈሉና የንግድ ፈቃድ አድሰው ያጠናቀቁ የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ልማት የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት እና የመልካም ሥራ አፈጻጸም ማስረጃዎች ያላቸው ለመሆኑ ዋናውንና ኮፒውን ማቅረብ የምትችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
 2. የግብር ክፍያ መለያ ቁጥር/ቲን/ሠርተፊኬት ማቅረብ የሚችል፣
 3. ተጫራቾች አሸናፊ በሆኑበት የንግድ ዘርፍ አሸናፊ የሆኑበትን ዕቃ የማስረከቢያ ቀን በተመለከተ እንዲሁም በጨረታው ዝርዝር ሰነድ ላይ የተጠየቀውን ዕቃ ለማቅረብ ከግራዋ ወረዳ ገንዘብና ትብብር /ቤት ጋር ሌላ ውል መፈጸም ይኖርባቸዋል፡፡
 4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ቢድ ቦንድ/ብር 5,000 ሺህ በጥሬ ገንዘብ ወይም በኢትዮጵያን ንግድ ባንክ በማስያዝ ሲፒኦ በማያያዝ ማስረጃቸውን ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት፡፡
 5. አነስተኛና ጥቃቅን ማህበራትን በተመለከተ ካደራቸው አካል ተደራጅተው ስለመሥራታቸው እንዲሁም የኢፌዴሪ ሚኒስትሮች ምክር ቤት ባወጣው ደንብ ቁጥር 201/2003 መሠረት መስፈርቱን ስለማሟላታቸው ማረጋገጫ ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
 6. የተዘጋጀውን ዝርዝር የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 100/ አንድ መቶ/ በመክፈል ከግራዋ ወረዳ ገቢዎች ባለሥልጣን /ቤት በአካል ቀርበው ሙግዛት ይችላሉ፡፡
 7. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ አሥራ አምስት የሥራ ቀናት አየር ላይ የሚቆይ ሲሆን በ15ኛው ቀን ከቀኑ በ11፡30 ሰዓት ተዘግቶ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 400 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ነገር ግን የመክፈቻው ቀን በዓል ወይም ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
 8. ተጫራቾች የመወዳደሪያው ዋጋ የተጨማሪ እሴት ታክስ ቫትን የሚጨምር ስለመሆኑና አለመሆኑ በዋጋ ማቅረቢያው ላይ በይፋ መግለጽ ይኖርባቸዋል፡፡
 9. ሌሎች ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
 10. ተጫራቾች አሸናፊ የሆኑባቸውን ዕቃዎች ማሸነፋቸው በይፋ ከተገለጸ ጀምሮ ባሉት 3 /ሦስት/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ከጽ/ቤታችን ጋር ሕጋዊ ውል በመፈራረም ውሉ በሚገልጸው መሠረት በጨረታው ሰነድ ላይ በተያያዘው ስፔስፊኬሽን መሠረት ያሸነፉባቸው የዕቃ ናሙናዎች እስከ /ቤታችን ድረስ በማቅረብ ትክክለኛነታቸውን ካረጋገጡ በኋላ የሚፈለገውን ዕቃ ሙሉ በሙሉ የማስረከብ ግዴታ አለባቸው፡፡ ከተጠየቀው ውጪ ማቅረብ በሕግ ያስጠይቃል፡፡
 11. ጨረታውን ያሸነፈ ተጫራች ለናሙና የሚያቀርባቸው ዕቃዎች ትክክለኛ መሆናቸው ከተረጋገጠ ከሚያቀርቡት ብዛት ውስጥ ተደምሮ ይታሰባል፡፡
 12. በጨረታው ተሸናፊ የሚሆኑ ተጫራቾች የጨረታው ውጤት ይፋ ከሆነበት ጀምሮ ባሉ 3 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ለጨረታው ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ሙሉ በሙሉ ይመለስላቸዋል፡፡
 13. የጨረታው አሸናፊ የሆነ ተጫራቾች አሸናፊ የሆነበትን ዕቃ በራሱ ወጪ ግራዋ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ልማት /ቤት ድረስ በማጓጓዝ አምጥተው በሞዴል 19 ገቢ ማድረጉ ከተረጋገጠ በኋላ በሚኖሩት 5 የሥራ ቀናት ክፍያ ይቀበላል፡፡
 14. ቢሮው የግዥውን መጠን እስከ 20 ፐርሰንት ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል፡፡
 15. ቢሮው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
 16. ስለ ጉዳዩ ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር፡0253340105/10 ደውሎ መጠየቅ ይችላል፡፡

የምሥራቅ ሐረርጌ ዞን ግራዋ ወረዳ ገንዘብ ኢኮኖሚ ትብብር ልማት ጽ/ቤት