ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የግል ድርጅቶች ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ ለዋና መ/ቤት ከዚህ በታች የቀረበውን
- አላቂ የቢሮ ዕቃዎች/የጽህፈት መሣሪያዎች/፣
- የጽዳት ዕቃዎች፣
- የሰራተኞች የደንብ ልብስ፣
- ልዩ ልዩ የቢሮ መሣሪያዎች፣
- የደንብ ልብስ ስፌት ፣
- የተሽከርካሪ ጎማና ቅባት እና
- የቴሌቪዥን ማስታወቂያ የፕሮዳክሽንና ስርጭት ስራ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መመዘኛዎች ማሟላት የሚችሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፍቃድ
- በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ የብቃት ማረጋገጫ መኖራቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
- በተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ግብር ከፋይነት የተመዘገቡና ማቅረብ የሚችሉ
- Tin No ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ከገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ማስረጃ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ
- ለጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተመሰከረለት CPO/ሲፒኦ/ወይም የባንክ ዋስትና በኤጀንሲው ስም ማስያዝ የሚችል
- ማንኛውም ተጫራች ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100/አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ለዚሁ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ መውሰድ ይችላሉ
- ተጫራቾች ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን ጠዋት 2፡30-6፡30 ከሰዓት ከ7፡30 – 11፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ ጨረታ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ የማወዳደሪያ ሰነዳቸውን ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ለቴሌቪዥን ማስታወቂያ የፕሮዳክሽንና ስርጭት ስራ ተጫራቾች ሰነዳቸውን ቴክኒካልና ፋይናንሽያል ለየብቻው ዋናውና ኮፒ በማለት ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ለሚጫረቱባቸው ዕቃዎች የቢሮ ዕቃዎች/የጽህፈት መሣሪያዎች፣ የጽዳት ዕቃዎች፣የሰራተኞች የደንብ ልብስ፣ ልዩ ልዩ የቢሮ መሣሪያዎች፣የተሽከርካሪ ጎማና ቅባት ናሙና/ሳምፕል/ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ንብረት ክፍል ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በ2/በሁለት/ ኢንቨሎፕ ዋናውና ኮፒ ብለው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ከጨረታው ከወጣበት ከ15ኛው ቀን በኋላ ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ 4፡15 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- የጨረታው መክፈቻ ቀን የእረፍት ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
- በጨረታው አሸንፎ በወቅቱ ውል ለማሰር ፍቃደኛ ያልሆነ ተጫራች የጨረታ ማሽነሪ ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ CPO/ሲፒኦ/ አይመለስም፡፡
- ኤጀንሲው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው፡፡
አድራሻችን ፡– አራት ኪሎ ከብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት በስተጀርባ የቀድሞ ሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር ሕንጻ
ለበለጠ ማብራሪያ፡– በስልክ ቁጥር 011 157 0333/0111550366
ተ.ቁ |
የግዥው ዓይነት |
የጨረታ ቁጥር |
የጨረታ ማስከበሪያ የገንዘብ መጠን |
ምርመራ |
ሎት1 |
አላቂ የቢሮ ዕቃዎች /የጽህፈትመሣሪያዎች/ |
001/2013 |
5,000/አምስት ሺህ ብር/ |
|
ሎት 2 |
የጽዳት ዕቃዎች ፣ |
002/2013 |
20,000 /ሃያ ሺህ ብር/ |
|
ሎት 3 |
ልዩ ልዩ የቢሮ መሣሪያዎች |
003/2013 |
2,000 /ሁለት ሺህ ብር/ |
|
ሎት 4 |
የሰራተኞች የደንብ ልብስ |
004/2013 |
10,000 /አስር ሺህ ብር/ |
|
ሎት 5 |
የደንብ ልብስ ስፌት |
005/2013 |
10,000 /አስር ሺህ ብር/ |
|
ሎት 6 |
የተሽከርካሪ ጎማና ቅባት |
006/2013 |
40,000 /አርባ ሺህ ብር/ |
|
ሎት 7 |
የቴሌቪዥን ማስታወቂያ የፕሮዳክሽንና ስርጭት ስራ |
007/2013 |
4000 /አራት ሺህ ብር/ |
|
የግል ድርጅቶች ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ