Cleaning and Janitorial Equipment and Service / Construction Machinery and Equipment / Garments and Uniforms / Materials / Office Furniture / Textile

የጋራ ጉሪ የመ/ደ/ት/ቤት የትምህርት እቃዎች ፣ የጽዳት እቃዎች ፣ የደንብ ልብስ፤ ፈርኒቸሮች፣ፕላንት ማሽነሪ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተደዳር በየካ /ከተማ ወረዳ 13 // ቤት የጋራ ጉሪ የመ///ቤት 2013 . የ1ኛ ሴሚስተር የትምህርት ዘመን ለስራ የሚያስፈልጉ እቃዎች ማለትም

 • ሎት 1 የትምህርት እቃዎች
 • ሎት 2 የጽዳት እቃዎች፣
 • ሎት 3 የደንብ ልብስ፤
 • ሎት 4 ፈርኒቸሮች
 • ሎት 5 ፕላንት ማሽነሪ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በጨረታው ለመሣተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች፡-

1. ለተጠቀሱት እቃዎች በዘርፉ የንግድ ስራ ላይ የተሰማሩ መሆን አለባቸው፤

 • 1.1. በዘመኑ/2013 የታደሰ ንግድ ፈቃድና በአቅራቢነት የተመዘገቡበት የምዝገባ ሰርተፊኬት ያላቸው የዘመኑን ግብር ስለመክፈላቸው ከሚመለከተው አካል ማረጃ ማቅረብ የሚችሉ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ከሆኑ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /ቲን ሰርተፊኬት/ ያላቸው፡፡
 • 12.ማንኛውምተጫራችከላይ የተዘረዘሩትን ሰነዶች ኦሪጅናልና ኮፒ ለየብቻ ከጨረታ ሰነዱ ጋር የማያያዝ በፖስታ በማሸግ ማስገባት አለበት፡፡ ተጫራቶች በአዲስ አበባ ከተማ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ድረ ገጽ በአቅራቢዎች በተዘጋጀው ክፍል የተመዘገቡ መሆን አለባቸው፡፡
 • ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ሰነድ /ቢድ ቦንድ/ የኢትዮጵያ ብር ሶስት ሺህ/3000/ ብር በባንክ የክፍያ ማዘዣ /ሲፒኦ/ ከኦሪጅናል ጨረታ ሰነዱ ጋር ታሽጎ መቅረብ አለበት፡፡
 1. ተጫራቾች በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር ተከታታይ የስራ ቀናት /ቤቱ ቢሮ ቁጥር 1 ማይመለስ /50/ሃምሳ ብር በመክፈል በመግዛት የሚጫረቱበት ዋጋ በሰነዱ ላይ በመሙላት ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ኮፒና ኦሪጂናል ለየብቻ ማስገባት አለባቸው፡፡
 2. ተጫራቾች ከሎት1  እስከ ሎት 5 መጫረት ወይም መርጠው አንዱን ወይም ሁለቱን መጫረት ይችላሉ ነገር ግን ከእያንዳንዱ ሎት እቃዎች መራርጦ ለተወሰኑት እቃዎች ብቻ ዋጋ ማቅረብ ተቀባይነት የለውም፡፡
 3.  የጨረታው ሳጥን በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአስር ተከታታይ የስራ ቀናት ክፍት ሆኖ በአስረኛ ቀን 830 (ስምንት ሰዓት ተኩል) ታሽጎ በእለቱ 900 (ዘጠኝ ሰዓት) ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በይፋ ይከፈታል፡፡
 4. /ቤቱ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
 5.  ተጨማሪ ማብራሪያ ለሚፈልጉ በአካል በማቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 0118932689 ደውለው መጠየቅ ይችላል፡፡
 • 2የጋራ ጉሪ 1 ደረጃ /ቤት በግልጽ ጨረታ የተለያዩ የጽዳት ዕቃ፣ የትምህርት እቃዎችና ደንብ ልብስ ፕላንት ማሽነሪ እና ፈርኒቸሮችን በሠንጠረዥ በቀረበው መሰረት የምትጫረቱበትን ዋጋ ሞልታችሁ እንድትወዳደሩ ይጋብዛል፡፡

1. የተጫራቾች መመሪያ

 • 1.2. ተጫራቾች በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፤የግብር ከፋይነት ሰርተፊኬት ፤የአቅራቢነት የምዝገባ ሠርተፊኬት ቫት ተመዝጋቢ ከሆኑ ሰርተፊኬት የዘመኑን ግብር ስለመክፈላቸው ከሚመለከተው አካል ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
 • 1.3. የተጫራቾች ከአንድ መቶ (100,000) ብር በላይ ዋጋ ያላቸው ዕቃዎች የሚጫረቱ ከሆነ የተእታ ቫት/ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡
 • 1.4. . 1.2 የተዘረዘሩትን ሠነዶች እያንዳንዳቸው ላይ ብቻ በአንድ ገጽ ላይ በግልጽ በሚነበብ ሁኔታ ኮፒ በማድረግ  በኦሪጂናሉ በማመሳከር ማስገባት አለባቸው፡፡
 • 15. የጨረታ ሰነድ በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጁ ሲሆን ከሎት 1 እስከ 5 የተዘረዘሩት ዕቃዎች በተዘረዘረው ሠንጠረዥ መሰረት የሚጫረቱበትን ዋጋ በትከክል በመሙላት መፈረም በሚገባቸው ቦታ ላይ በመፈረም በማህተም ቦታ ማህተማቸውን በማድረግ በሰም በታሸገ ፖስታ ማስገባት አለባቸው፡፡
 • 1.6 /ቤቱ ያዘጋጀው የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ትተው በሌላ በራሳቸው ሰነድ ዋጋ የሚያቀርቡ ተጫራቾች ከጨረታ ውጭ ይሆናሉ፡፡
 • 1.7. ተጫራቾች ናሙና ያቀርባል ተብለው የተዘረዘሩትን እቃዎች ጨረታ ከመዘጋቱ በፊት በማቅረብ በማስመዝገብ ማስረከብ አለባቸው፡
 • 1.8. ናሙናዎች ለተሸናፊ ተጫራቾች አሸናፊው እንደተገለጸ ይመለስላቸዋል፡፡ ለአሸናፊው ተጫራች ግን ዕቅዎችን አስረክቦ እስኪጠናቀቅ ድረስ ለማመሳከሪያነት ቆይተው አስረክቦ ሲጨርስ ተመላሽ ይሆናል፡፡
 • 1.9 የጨረታ ሣጥኑ /ቤት የሚገኝ ሲሆን ተጫራቾች የጨረታ ማስገቢያ ቀንና ሰዓት ከመጠናቀቁ በፊት በስራ ቀንና ሰዓት ሰነዶቻቸውን ማስገባት አለባቸው፡፡
 • 1.10. ቤቱ የጨረታው ኮሚቴ/እቃዎቹን የሚመረጠው ዝቅተኛ ዋጋ በማየት ብቻ ሳይሆን ጥራትን መሰረት ያደረገ መሆኑን በመገንዘብ ናሙና ሲያቀርቡ ጥራቱን የጠበቀ እቃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
 • 1.11. በጨረታው ሰነድ ላይ ግልፅ ያልሆኑ ጉዳዮችን ማብራሪያ የሚፈልጉ በጽሁፍ ወይም በአካል በስራ ቀንና ሰዓት በት/ቤቱ በመገኘት ወይም በስልከ 0118932689 መጠየቅ ይችላሉ

1.2. ከተገለፀው ቀንና ሰዓት በኋላ የሚመጡ ተጫራቾች አይስተናገዱም፡፡

 • 1.2.ተጫራቾች የጨረታ ማስከበርያ /ቢድ ቦንድ/ የኢትዮጽያ ብር 3 በባንካ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ለት/ቤቱ ማስያዝ አለባቸው፡፡ የጨረታ ማስከበርያ ለአሸናፊ ተጫራቾች አሸናፊው እንደተገለጸ ይመለስላቸዋል፡፡
 • 13. አሸናፊ ተጫራች ለውል ማስከበሪያ ከጠቅላላው የውል ዋጋ 10 ፐርሰንት የማስያዝ ግዴ ስላለበት የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ/ የኢትዮጵያ ብር 3 ለውል ማስከበርያ ይደመርለታል፡፡
 • 1.14. ተጫራቾች የማጭበርበር እና ሙስናን ላለመፈፀሙ ከጨረታ ሰነድ ጋር የተያያዘውን ቅጽ መፈረም አላባቸው፡፡
 • 1.15 የጨረታ ሂደቱን ለማዛባት መሞከር ከጨረታ ውጭ ከማድረጉም በተጨማሪ ለወደፊት በመንግስት ግዥ እንዳይሳተፍ ያደርጋል፡፡
 • 1.16. አሸናፊው ድርጅት ማሸነፉ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ10  ቀናት ውስጥ ቀርቦ ውል መፈረም አለበት፡፡
 • 1.16.1. አሸናፊው ድርጅት ውል ከፈረመ በኋላ ከጠቅላላው የውል ዋጋ 30 ፐርሰንት ቅድመ ክፍያ ይፈፀምለታል፡፡ በውል አፈፃፀም ወቅት ከገበያ ዋጋ መቀነሱ ምክንያት አሸናፊው ድርጅት የዋጋ ቅናሽ ማድረግ ይችላል፡፡ /ቤቱ ግን የዋጋ ጭማሪ ማድረግ አይችሉም፡፡

17. አሸናፊው ድርጅት በውል መሰረት ግዴታውን ሳይፈፅም ከቀረ ውል ማስከበሪያው ይወረሳል፡፡

18. አሸናፊው ድርጅት ለቅድመ ክፍያው ተመጣጣኝ ዋስትና ከታወቀ ስንከ የሚሰጥቼክ ወይም በሁኔታ ላይ የተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማቅረብ አለበት፡፡

ማሳሰቢያ:- በዋናነት ማንኛውም ተጫራች በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የግዢ አፈፃፀም መመሪያ ቁጥር 3/2002 ባወጣው መሰረት የሚስተናገድ መሆኑን አንብቦ እና ተረድቶ መምጣት አለበት፡

 

በአዲስ አበባ አስተዳደር በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 13 ት/ጽ/ቤት ጋራ ጉሪ የመ//ት/ቤት